1 ሳሙኤል 20:35 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲህም ሆነ በነጋው ዮናታን ከዳዊት ጋር ምልክት ለማድረግ ወደ ተቃጠረበት ቦታ ወደ ሜዳ ወጣ፤ ከእርሱም ጋር ታናሽ ብላቴና ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በማግስቱም ጧት ዮናታን አንድ ትንሽ ልጅ አስከትሎ፣ ከዳዊት ጋራ ወደ ተቃጠረበት ቦታ ሄደ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በማግስቱ ጠዋት ዮናታን አንድ ትንሽ ልጅ አስከትሎ፥ ከዳዊት ጋር ወደ ተቃጠረበት ቦታ ሄደ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በማግስቱ ጠዋት በቀጠሮአቸው መሠረት ዮናታን ዳዊትን ለማግኘት ወደ ሜዳ ሄደ፤ ሲሄድም አንድ ትንሽ ልጅ አስከትሎ ነበር፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲህም ሆነ፥ በነጋው ዮናታን ከዳዊት ጋር ወደ ተቃጠረበት ቦታ ወደ ሜዳ ወጣ፥ ከእርሱም ጋር ታናሽ ብላቴና ነበረ። |
ሦስት ቀንም ያህል ቈይ፤ ከዚህም በኋላ በፈለገህ ጊዜ ትመጣና ነገሩ በተደረገበት ቀን በተሸሸግህበት ስፍራ ትቀመጣለህ፤ በኤርገብ ድንጋይም አጠገብ ቈይ።
አባቱ በእርሱ ላይ ክፉ ነገርን ሊያደርግ ስለ ቈረጠ ዮናታን ስለ ዳዊት አዝኖአልና እጅግ ተቈጥቶ ከማዕዱ ተነሣ፤ በመባቻውም በሁለተኛው ቀን ግብር አልበላም።
ብላቴናውንም፥ “ሮጠህ የምወረውራቸውን ፍላጻዎች ፈልግልኝ” አለው። ብላቴናውም በሮጠ ጊዜ ዮናታን ፍላጻውን ወደ ማዶ አሳልፎ ወረወረው።