La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ሳሙኤል 20:34 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

አባቱ በእ​ርሱ ላይ ክፉ ነገ​ርን ሊያ​ደ​ርግ ስለ ቈረጠ ዮና​ታን ስለ ዳዊት አዝ​ኖ​አ​ልና እጅግ ተቈ​ጥቶ ከማ​ዕዱ ተነሣ፤ በመ​ባ​ቻ​ውም በሁ​ለ​ተ​ኛው ቀን ግብር አል​በ​ላም።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ዮናታንም በታላቅ ቍጣ ከግብሩ ላይ ተነሣ፤ አባቱም ዳዊትን ስላዋረደው ወሩ በገባ በሁለተኛው ቀን ምግብ አልበላም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ዮናታንም በታላቅ ቁጣ ከግብሩ ላይ ተነሣ፤ አባቱም ዳዊትን ስላዋረደው ወሩ በገባ በሁለተኛው ቀን ምግብ አልበላም።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ዮናታንም በቊጣ ከማእዱ ላይ ተነሣ፤ በዚያ ቀን ማለትም አዲስ ጨረቃ በታየችበት በዓል በሁለተኛ ቀን ምንም ምግብ አልበላም፤ ሳኦል ዳዊትን በማዋረዱ ምክንያት ስለ ዳዊት ሁኔታ ዮናታን በብርቱ አዝኖ ነበር።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

አባቱ ዳዊትን ስላሳፈረው ዮናታን ስለ ዳዊት አዝኖአልና እጅግ ተቆጥቶ ከሰደቃው ተነሣ፥ በመባቻውም በሁለተኛ ቀን ግብር አልበላም።

Ver Capítulo



1 ሳሙኤል 20:34
5 Referencias Cruzadas  

በም​ድር ላይም መል​ካ​ምን የሚ​ሠራ ኀጢ​አ​ት​ንም የማ​ያ​ደ​ርግ ጻድቅ ሰው አይ​ገ​ኝ​ምና።


ስለ ልባቸውም ድንዛዜ አዝኖ ዙሪያውን እየተመለከተ በቍጣ አያቸው፤ ሰውየውንም “እጅህን ዘርጋ፤” አለው። ዘረጋትም፤ እጁም ዳነች።


ተቈጡ፤ አት​በ​ድ​ሉም፤ ፀሐይ ሳይ​ጠ​ል​ቅም ቍጣ​ች​ሁን አብ​ርዱ።


ሳኦ​ልም ሊገ​ድ​ለው በዮ​ና​ታን ላይ ጦሩን አነሣ፤ ዮና​ታ​ንም አባቱ ዳዊ​ትን ይገ​ድ​ለው ዘንድ ያች ክፉ ነገር እንደ ተቈ​ረ​ጠች ዐወቀ።


እን​ዲ​ህም ሆነ በነ​ጋው ዮና​ታን ከዳ​ዊት ጋር ምል​ክት ለማ​ድ​ረግ ወደ ተቃ​ጠ​ረ​በት ቦታ ወደ ሜዳ ወጣ፤ ከእ​ር​ሱም ጋር ታናሽ ብላ​ቴና ነበረ።