1 ሳሙኤል 20:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከመባቻም በኋላ በማግሥቱ በሁለተኛው ቀን የዳዊት ስፍራ ባዶውን ነበረ፤ ሳኦልም ልጁን ዮናታንን፥ “የእሴይ ልጅ ትናትና ዛሬ ወደ ግብር ያልመጣ ስለምን ነው?” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በማግስቱም፣ ወር በገባ በሁለተኛው ቀን የዳዊት መቀመጫ ባዶ ነበር፤ ከዚያም ሳኦል ልጁን ዮናታንን፣ “የእሴይ ልጅ ትናንትናም፣ ዛሬም ግብር ላይ ያልተገኘው ለምንድን ነው?” ሲል ጠየቀው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በማግስቱም፥ ወር በገባ በሁለተኛው ቀን የዳዊት መቀመጫ ባዶ ነበር፤ ከዚያም ሳኦል ልጁን ዮናታንን፥ “የእሴይ ልጅ ትናንትናም፥ ዛሬም ግብር ላይ ያልተገኘው ለምንድን ነው?” ሲል ጠየቀው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አዲስ ጨረቃ የታየችበት በዓል ካለፈ በኋላም በተከታዩ ቀን የዳዊት ወንበር ባዶ ነበር፤ ስለዚህ ሳኦል ልጁን ዮናታንን “የእሴይ ልጅ ትናንትም፥ ዛሬም ወደዚህ ግብዣ ያልመጣው ስለምንድን ነው?” ሲል ጠየቀው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከመባቻም በኋላ በማግሥቱ በሁለተኛው ቀን የዳዊት ስፍራ ባዶውን ነበረ፥ ሳኦልም ልጁን ዮናታንን፦ የእሴይ ልጅ ትናንትና ወይም ዛሬ ግብር ሊበላ ያልመጣ ስለ ምን ነው? አለው። |
ሳኦልም፥ “አንድ ነገር ሆኖ ይሆናል፤ ምንአልባትም ንጹሕ አይደለም ይሆናል፤ በእውነትም ንጹሕ አይደለም” ብሎ አስቦአልና በዚያ ቀን ምንም አልተናገረም።
ዳዊትም ዮናታንን አለው፥ “እነሆ ነገ መባቻ ነው፤ በንጉሥም አጠገብ ለምሳ አልቀመጥም፤ እስከ ማታ ድረስ በውጭ በሜዳ እንድሸሸግ አሰናብተኝ ።
ናባልም ተነሥቶ ለዳዊት ብላቴኖች መለሰላቸው እንዲህም አላቸው፥ “ዳዊት ማን ነው? የእሴይስ ልጅ ማን ነው? እያንዳንዳቸው ከጌቶቻቸው የኰበለሉ አገልጋዮች ዛሬ ብዙ ናቸው።