1 ሳሙኤል 2:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ብላቴናው ሳሙኤልም አደገ፤ በእግዚአብሔርም በሰውም ፊት ሞገስ እያገኘ ሄደ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ብላቴናውም ሳሙኤል በአካልና በሞገስ በእግዚአብሔርና በሰው ፊት እያደገ ሄደ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ብላቴናው ሳሙኤልም እያደገና፥ በጌታም በሰውም ፊት ሞገስ እያገኘ ሄደ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወጣቱ ሳሙኤል ግን በቁመት እያደገ፥ በእግዚአብሔርና በሰውም ዘንድ ጸጋና ሞገስን እያገኘ ሄደ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ብላቴናውም ሳሙኤል እያደገ ሄደ፥ በእግዚአብሔርም በሰውም ፊት ሞገስ እያገኘ ሄደ። |
እግዚአብሔርንም ያመሰግኑ ነበር፤ በሕዝቡም ሁሉ ዘንድ መወደድ ነበራቸው፤ እግዚአብሔርም የሚድኑትን ዕለት ዕለት በእነርሱ ላይ ይጨምር ነበር።
እግዚአብሔርም ሐናን ጐበኘ፤ ዳግመኛም ፀነሰች፥ ሦስት ወንዶችና ሁለት ሴቶች ልጆችን ወለደች። ብላቴናው ሳሙኤልም በእግዚአብሔር ፊት አደገ።