1 ሳሙኤል 17:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእኔም ጋር ሊዋጋ ቢችል ቢገድለኝም፥ ባሪያዎች እንሆናችኋለን፤ እኔ ግን ባሸንፈው፥ ብገድለውም፥ እናንተ ባሪያዎች ትሆኑናላችሁ፤ ለእኛም ትገዛላችሁ” አለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከእኔ ጋራ ሊዋጋና ሊገድለኝ ከቻለ፣ እኛ ባሪያዎቻችሁ እንሆናለን፤ እኔ ባሸንፈውና ብገድለው ግን እናንተ ባሪያዎቻችን ትሆናላችሁ፤ ትገዙልናላችሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእኔ ጋር ሊዋጋና ሊገድለኝ ከቻለ፥ እኛ ባርያዎቻችሁ እንሆናለን፤ እኔ ባሸንፈውና ብገድለው ግን እናንተ ባርያዎቻችን ትሆናላችሁ፤ ትገዙልናላችሁ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱ እኔን አሸንፎ ከገደለኝ፥ እኛ የእናንተ ባሪያዎች ሆነን እንገዛላችኋለን፤ ነገር ግን እኔ አሸንፌ ከገደልኩት፥ እናንተ የእኛ ባርያዎች ሆናችሁ ትገዙልናላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእኔም ጋር ሊዋጋ ቢችል ቢገድለኝም፥ ባሪያዎች እንሆናችኋለን፥ እኔ ግን ባሸንፈው ብገድለውም፥ እናንተ ባሪያዎች ትሆኑናላችሁ፥ ለእኛም ትገዛላችሁ አለ። |
እንዲህም ሆነ፤ ከአንድ ወር በኋላ አሞናዊው ናዖስ መጣ፤ በኢያቢስ ገለዓድም ሰፈረ፤ የኢያቢስም ሰዎች ሁሉ፥ “አሞናዊውን ናዖስን ቃል ኪዳን አድርግልን፤ እኛም እንገዛልሃለን” አሉት።
ፍልስጥኤማዊውም፥ “ዛሬ የእስራኤልን ጭፍሮች ተገዳደርኋቸው፤ አንድ ሰው ስጡኝ ሁለታችንም ለብቻችን እንዋጋ አልኋቸው” አለ።