1 ሳሙኤል 17:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሳኦልና የእስራኤልም ሰዎች ሁሉ ከፍልስጥኤማውያን ጋር እየተዋጉ በኤላ ሸለቆ ነበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነርሱ ከሳኦልና ከእስራኤል ሰዎች ሁሉ ጋራ ሆነው በኤላ ሸለቆ ከፍልስጥኤማውያን ጋራ እየተዋጉ ናቸው።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱ ከሳኦልና ከእስራኤል ሰዎች ሁሉ ጋር ሆነው በዔላ ሸለቆ ከፍልስጥኤማውያን ጋር እየተዋጉ ናቸው።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሥ ሳኦል፥ ወንድሞችህና መላው እስራኤላውያን በኤላ ሸለቆ ከፍልስጥኤማውያን ጋር በመዋጋት ላይ ናቸው።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሳኦልና እነርሱ የእስራኤልም ሰዎች ሁሉ ከፍልስጥኤማውያን ጋር እየተዋጉ በዔላ ሸለቆ ነበሩ። |
ዳዊትም ማልዶ ተነሣ፤ በጎቹንም ለጠባቂ ተወ፤ እሴይም ያዘዘውን ይዞ ሄደ፤ ጭፍራውም ተሰልፎ ሲወጣ፥ ለሰልፍም ሲጮኽ በሰረገሎች ወደ ተከበበው ሰፈር መጣ።