አባታቸው እስራኤልም እንዲህ አላቸው፥ “ነገሩ እንዲህ ከሆነስ ይህን አድርጉ ፤ ከምድሩ ፍሬ በዓይበታችሁ ይዛችሁ ሂዱ፤ ለዚያም ሰው እጅ መንሻ፥ ጥቂት በለሳን፥ ጥቂት ማር፥ ሽቱ፥ ዕጣን፥ ተምር፥ ለውዝ ውሰዱ።
1 ሳሙኤል 16:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እሴይም እንጀራና የወይን ጠጅ አቁማዳ የተጫነ አህያ፥ አንድም የፍየል ጠቦት ወስዶ በልጁ በዳዊት እጅ ወደ ሳኦል ላከ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እሴይም እንጀራና በወይን ጠጅ የተሞላ አቍማዳ በአህያ አስጭኖ፣ የፍየል ጠቦትም አስይዞ ልጁን ዳዊትን ወደ ሳኦል ላከው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እሴይም እንጀራና በወይን ጠጅ የተሞላ አቁማዳ በአህያ አስጭኖ፥ የፍየል ጠቦትም አስይዞ ልጁን ዳዊትን ወደ ሳኦል ላከው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እሴይም ዳዊትን አንድ ትንሽ የፍየል ጠቦት አስይዞ፥ እንጀራና የወይን ጠጅ የተሞላበት አቁማዳ ከተጫነ አንድ አህያ ጋር ወደ ሳኦል ላከው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እሴይም እንጀራና የወይን ጠጅ አቁማዳ የተጫነ አህያ የፍየልም ጠቦት ወስዶ በልጁ በዳዊት እጅ ወደ ሳኦል ላከ። |
አባታቸው እስራኤልም እንዲህ አላቸው፥ “ነገሩ እንዲህ ከሆነስ ይህን አድርጉ ፤ ከምድሩ ፍሬ በዓይበታችሁ ይዛችሁ ሂዱ፤ ለዚያም ሰው እጅ መንሻ፥ ጥቂት በለሳን፥ ጥቂት ማር፥ ሽቱ፥ ዕጣን፥ ተምር፥ ለውዝ ውሰዱ።
አቤግያም ፈጥና፦ ሁለት መቶ እንጀራ፥ ሁለት አቁማዳ የወይን ጠጅ፥ አምስት የተዘጋጁ በጎች፥ አምስትም መስፈሪያ በሶ፥ አንድ ጎሞር ዘቢብ፥ ሁለት መቶም የበለስ ጥፍጥፍ ወሰደች፥ በአህዮችም ላይ አስጫነች።