ሙሴም እግዚአብሔርን፥ “ወደ ግብፅ ንጉሥ ወደ ፈርዖን እሄድ ዘንድ፥ የእስራኤልንም ልጆች ከግብፅ ምድር አወጣ ዘንድ እኔ ማን ነኝ?” አለው።
1 ሳሙኤል 16:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሳሙኤልም፥ “እንዴት እሄዳለሁ? ሳኦል ቢሰማ ይገድለኛል” አለ። እግዚአብሔርም፥ “አንዲት ጊደር ይዘህ ሂድና፦ ‘ለእግዚአብሔር እሠዋ ዘንድ መጣሁ’ በል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሳሙኤል ግን፣ “ሳኦል ከሰማ ስለሚገድለኝ እንዴት መሄድ እችላለሁ?” አለ። እግዚአብሔርም እንዲህ አለው፤ “አንዲት ጊደር ይዘህ ሂድና፣ ‘ለእግዚአብሔር ልሠዋ መጥቻለሁ’ በል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሳሙኤል ግን፥ “ሳኦል ከሰማ ስለሚገድለኝ እንዴት መሄድ እችላለሁ?” አለ። ጌታም እንዲህ አለው፤ “አንዲት ጊደር ይዘህ ሂድና፥ ‘ለጌታ ልሠዋ መጥቻለሁ’ በል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሳሙኤልም “ይህን ለማድረግ እንዴት ይቻለኛል? ሳኦል ይህን ቢሰማ ይገድለኛል!” ሲል ጠየቀ። እግዚአብሔርም እንዲህ ሲል መለሰለት፤ “ ‘ለእግዚአብሔር መሥዋዕት ለማቅረብ መጥቻለሁ’ ብለህ ጊደር ይዘህ ሂድ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሳሙኤልም፦ እንዴት እሄዳለሁ? ሳኦል ቢሰማ ይገድለኛል አለ። እግዚአብሔርም፦ አንዲት ጊደር ይዘህ ሂድና፦ ለእግዚአብሔር እሠዋ ዘንድ መጣሁ በል። |
ሙሴም እግዚአብሔርን፥ “ወደ ግብፅ ንጉሥ ወደ ፈርዖን እሄድ ዘንድ፥ የእስራኤልንም ልጆች ከግብፅ ምድር አወጣ ዘንድ እኔ ማን ነኝ?” አለው።
እርሱም፥ “ዘመዶቼ በከተማ ውስጥ መሥዋዕት አላቸውና፥ ወንድሞቼም ጠርተውኛልና እባክህ! አሰናብተኝ፤ አሁንም በዐይኖችህ ሞገስ አግኝቼ እንደ ሆነ ልሂድና ወንድሞቼን ልይ አለ፤ ስለዚህ ወደ ንጉሥ ማዕድ አልመጣም” ብሎ መለሰለት።
ቈነጃጅቱም፥ “አዎን እነሆ፥ በፊታችሁ ነው። ዛሬ ወደ ከተማዪቱ መጥቶአልና፥ ዛሬም ሕዝቡ በባማ ኮረብታ ላይ መሥዋዕት ማቅረብ አለባቸውና።