ዮሴፍም በግብፅ ንጉሥ በፈርዖን ፊት በቆመ ጊዜ ዕድሜው ሠላሳ ዓመት ነበረ። ዮሴፍም ከፈርዖን ፊት ወጣ፤ የግብፅ ምድርንም ሁሉ ዞረ።
1 ሳሙኤል 16:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አገልጋዮችህ በፊትህ ይናገሩ፤ በበገና የሚዘምር ሰውም ለጌታቸው ይፈልጉለት፤ ክፉ መንፈስም በመጣብህ ጊዜ በገናውን ሲመታ አንተ ደኅና ትሆናለህ፤ እርሱም ያሳርፍሃል” አሉት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንግዲህ በገና መደርደር የሚችል ሰው እንዲፈልጉ፣ ጌታችን በፊቱ የሚቆሙትን አገልጋዮቹን ይዘዝ፤ ከዚያም ከእግዚአብሔር የታዘዘው ክፉ መንፈስ ባንተ ላይ በሚመጣ ጊዜ በገና ይደረድርልሃል፤ ደኅናም ትሆናለህ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንግዲህ በገና መደርደር የሚችል ሰው እንዲፈልጉ፥ ጌታችን በፊቱ የሚቆሙትን አገልጋዮቹን ይዘዝ፤ ከዚያም ከእግዚአብሔር የታዘዘው ክፉ መንፈስ ባንተ ላይ በሚመጣ ጊዜ በገና ይደረድርልሃል፤ ደኅናም ትሆናለህ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ንጉሥ ሆይ! በገና መደርደር የሚያውቅ ሰው ፈልገን እንድናመጣልህ እዘዘን፤ ከዚያም በኋላ ክፉ መንፈስ በሚመጣብህ ጊዜ ያ ሰው በገና ይደረድርልሃል፤ አንተም እንደገና ጤናማ ትሆናለህ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በገና መልካም አድርጎ የሚመታ ሰው ይሹ ዘንድ ጌታችን በፊቱ የሚቆሙትን ባሪያዎቹን ይዘዝ፥ ከእግዚአብሔርም ዘንድ ክፉ መንፈስ በሆነብህ ጊዜ በእጅ ሲመታ አንተ ደኅና ትሆናለህ አሉት። |
ዮሴፍም በግብፅ ንጉሥ በፈርዖን ፊት በቆመ ጊዜ ዕድሜው ሠላሳ ዓመት ነበረ። ዮሴፍም ከፈርዖን ፊት ወጣ፤ የግብፅ ምድርንም ሁሉ ዞረ።
ሚስቶችህ የተመሰገኑ ናቸው፤ በፊትህ ሁልጊዜ የሚቆሙ፥ ጥበብህን የሚሰሙ እነዚህ አገልጋዮችህም ምስጉኖች ናቸው።
ከዚያም በኋላ የፍልስጥኤማውያን ጭፍራ ወዳለበት ወደ እግዚአብሔር ኮረብታ ትመጣለህ፤ በዚያም ፍልስጥኤማዊው ናሴብ አለ፤ ወደዚያም ወደ ከተማዪቱ በደረስህ ጊዜ በገናና ከበሮ፥ እምቢልታና መሰንቆ ይዘው ትንቢት እየተናገሩ ከኰረብታው መስገጃ የሚወርዱ የነቢያትን ጉባኤ ታገኛለህ።
እንዲህም ሆነ፤ በነጋው ሳኦልን ክፉ መንፈስ ከእግዚአብሔር ዘንድ ያዘው፤ በቤቱም ውስጥ ትንቢት ተናገረ። ዳዊትም በየቀኑ ያደርግ እንደ ነበረ በእጁ በገና ይመታ ነበር። ሳኦልም ጦሩን በእጁ ይዞ ነበር።