አብርሃምም ማልዶ ተነሣ፤ እንጀራንም ወሰደ፤ የውኃ አቍማዳንም ለአጋር በትከሻዋ አሸከማት፤ ሕፃኑንም ሰጥቶ አስወጣት፤ እርስዋም ሄደች፤ በዐዘቅተ መሐላም በኩል ባለው ምድረ በዳ ተቅበዘበዘች።
1 ሳሙኤል 15:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሳሙኤልም እስራኤልን ለመገናኘት በጥዋት ገሥግሦ ሄደ። ለሳሙኤልም፥ “ሳኦል ወደ ቀርሜሎስ መጣ፤ እነሆም፥ ለራሱ የመታሰቢያ ዐምድ አቆመ” ብለው ነገሩት። ሳሙኤልም ሰረገላውን መልሶ ወደ ጌልጌላ ወደ ሳኦል ወረደ፤ ከአማሌቅ ዘንድ ከአመጣውም ከአማረው ከምርኮው መንጋ ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መሥዋዕት ሲሠዋ አገኘው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሳሙኤልም ጧት ተነሥቶ በማለዳ ሳኦልን ለመገናኘት ሄደ፤ ነገር ግን፣ “ሳኦል ወደ ቀርሜሎስ ሄዷል፤ ለራሱ ክብር የመታሰቢያ ሐውልት በዚያ ካቆመ በኋላ ተመልሶ ወደ ጌልገላ ወርዷል” ተብሎ ተነገረው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሳሙኤልም ጠዋት ተነሥቶ በማለዳ ሳኦልን ለመገናኘት ሄደ፤ ነገር ግን፥ “ሳኦል ወደ ቀርሜሎስ ሄዷል፤ ለራሱ ክብር የመታሰቢያ ሐውልት በዚያ ካቆመ በኋላ ተመልሶ ወደ ጌልገላ ወርዷል” ተብሎ ተነገረው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በማግስቱም ማለዳ በመነሣት ሳኦልን ፈልጎ ለማግኘት ሄደ፤ ሳኦል ለራሱ ሐውልት ወዳቆመባት ወደ ቀርሜሎስ ከተማ ከደረሰ በኋላ ተመልሶ ወደ ጌልጌላ መሄዱን ሰማ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሳሙኤልም በነጋው ሳኦልን ለመገናኘት ማለደ፦ ሳኦልም ወደ ቀርሜሎስ መጣ፥ እነሆም፥ የመታሰቢያ ዓምድ ባቆመ ጊዜ ዞሮ አለፈ፥ ወደ ጌልገላም ወረደ የሚል ወሬ ለሳሙኤል ደረሰለት። |
አብርሃምም ማልዶ ተነሣ፤ እንጀራንም ወሰደ፤ የውኃ አቍማዳንም ለአጋር በትከሻዋ አሸከማት፤ ሕፃኑንም ሰጥቶ አስወጣት፤ እርስዋም ሄደች፤ በዐዘቅተ መሐላም በኩል ባለው ምድረ በዳ ተቅበዘበዘች።
አቤሴሎምም በሕይወቱ ሳለ፥ “ለስሜ መታሰቢያ የሚሆን ልጅ የለኝም” ብሎ ሐውልት ወስዶ በንጉሥ ሸለቆ ውስጥ ለራሱ በስሙ አቁሞ ነበር፤ ያችም ሐውልት እስከ ዛሬ ድረስ “እደ አቤሴሎም” ተብላ ትጠራለች።
አክዓብም ሊበላና ሊጠጣ ወጣ። ኤልያስም ወደ ቀርሜሎስ አናት ወጣ፤ ፊቱንም በጕልበቱ መካከል አቀርቅሮ በግንባሩ ወደ ምድር ተደፋ።
በምድረ በዳውም ግንቦችን ሠራ፤ ብዙ ጕድጓድም ማሰ፤ በቆላውና በደጋው ብዙ እንስሶች ነበሩትና፤ ደግሞም እርሻ ይወድድ ነበርና በተራራማውና በፍሬያማው ስፍራ አራሾችና የወይን አትክልተኞች ነበሩት።
ስለዚህ፦ ፍልስጥኤማውያን አሁን ወደ እኔ ወደ ጌልጌላ ይወርዱብኛል፤ እኔም የእግዚአብሔርን ፊት አልለመንሁም አልሁ፤ ስለዚህም ደፍሬ የሚቃጠል መሥዋዕትን አሳረግሁ” አለ።
ሳሙኤልም ከጌልጌላ ተነሥቶ መንገዱን ሄደ፤ የቀሩትም ሕዝብ ሳኦልን ተከትለው ሰልፈኞቹን ሊገናኙ ሄዱ። ከጌልጌላም ተነሥተው ወደ ብንያም ገባዖን መጡ፤ ሳኦልም ከእርሱ ጋር የነበሩትን ሕዝብ ቈጠረ፤ ስድስት መቶም የሚያህሉ ሰዎች ነበሩ።
ዳዊትም ማልዶ ተነሣ፤ በጎቹንም ለጠባቂ ተወ፤ እሴይም ያዘዘውን ይዞ ሄደ፤ ጭፍራውም ተሰልፎ ሲወጣ፥ ለሰልፍም ሲጮኽ በሰረገሎች ወደ ተከበበው ሰፈር መጣ።
በማዖንም የተቀመጠ አንድ ሰው ነበረ፤ ከብቱም በቀርሜሎስ ነበረ፤ እጅግም ታላቅ ሰው ነበረ፤ ለእርሱም ሦስት ሺህ በጎችና አንድ ሺህ ፍየሎች ነበሩት፤ በቀርሜሎስም በጎቹን ሊሸልት ሄደ።
ሳሙኤልም አንድ ድንጋይ ወስዶ በመሴፋና በአሮጌው ከተማ መካከል አኖረው፤ ስሙንም፥ “እስከ አሁን ድረስ እግዚአብሔር ረድቶናል” ሲል “አቤንኤዜር” ብሎ ጠራው። እብነ ረድኤት ማለት ነው።