ኤልሳዕም፥ “የእግዚአብሔርን ቃል ስማ፤ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ነገ በዚህ ጊዜ በሰማርያ በር፥ ሁለት መስፈሪያ ገብስ በአንድ ሰቅል አንድ መስፈሪያ መልካም ዱቄትም በአንድ ሰቅል ይሸመታል” አለው።
1 ሳሙኤል 15:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሳሙኤልም ሳኦልን አለው፥ “በእስራኤል ላይ ንጉሥ እንድትሆን እቀባህ ዘንድ እግዚአብሔር ላከኝ፤ አሁንም የእግዚአብሔርን ቃል ስማ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሳሙኤል ሳኦልን እንዲህ አለው፤ “በሕዝቡ በእስራኤል ላይ ቀብቼ እንዳነግሥህ፣ እግዚአብሔር የላከው እኔን ነው፤ ስለዚህ የእግዚአብሔርን ድምፅ አሁን ስማ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሳሙኤል ሳኦልን እንዲህ አለው፤ “በሕዝቡ በእስራኤል ላይ ንጉሥ እንድትሆን እንድቀባህ ጌታ ላከኝ፤ አሁንም የጌታን ቃል ስማ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሳሙኤል ሳኦልን እንዲህ አለው፤ “በሕዝቡ በእስራኤል ላይ ቀብቼ እንዳነግሥህ እግዚአብሔር የላከኝ እኔ ነኝ፤ አሁንም ሁሉን የሚችል እግዚአብሔር የሚለውን ስማ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሳሙኤልም ሳኦልን አለው፦ በሕዝቡ በእስራኤል ላይ ንጉሥ እንድትሆን እቀባህ ዘንድ እግዚአብሔር ላከኝ፥ አሁንም የእግዚአብሔርን ድምፅ ስማ። |
ኤልሳዕም፥ “የእግዚአብሔርን ቃል ስማ፤ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ነገ በዚህ ጊዜ በሰማርያ በር፥ ሁለት መስፈሪያ ገብስ በአንድ ሰቅል አንድ መስፈሪያ መልካም ዱቄትም በአንድ ሰቅል ይሸመታል” አለው።
ሳሙኤልም የዘይቱን ቀንድ ወስዶ በራሱ ላይ አፈሰሰው፤ ሳመውም፤ እንዲህም አለው፥ “በሕዝቡ በእስራኤል ላይ ትነግሥ ዘንድ እግዚአብሔር ቀብቶሃል፤ የእግዚአብሔርንም ሕዝብ ትገዛለህ፤ በዙሪያውም ካሉ ጠላቶቻቸው እጅ ታድናቸዋለህ። እግዚአብሔርም በርስቱ ላይ ትነግሥ ዘንድ እንደ ቀባህ ምልክቱ ይህ ነው።
እግዚአብሔርን ብትፈሩ፥ ብታመልኩትም፥ ቃሉንም ብትሰሙ፥ በእግዚአብሔርም ትእዛዝ ላይ ባታምፁ፥ እናንተና በእናንተ ላይ የነገሠው ንጉሥ አምላካችሁን እግዚአብሔርን ብትከተሉ፥ መልካም ይሆንላችኋል።
ሳሙኤልም ሳኦልን፥ “በድለኻል፤ አምላክህ እግዚአብሔር ያዘዘህን ትእዛዙን አልጠበቅህምና፤ ዛሬ እግዚአብሔር መንግሥትህን በእስራኤል ላይ ለዘለዓለም አጽንቶልህ ነበር።
እንዲህም አለው፥ “ነገ በዚህች ሰዓት ከብንያም ሀገር አንድ ሰው እልክልሃለሁ፤ ልቅሶአቸው ወደ እኔ ስለ ደረሰ የሕዝቤን ሥቃያቸውን ተመልክችአለሁና ለሕዝቤ ለእስራኤል አለቃ ይሆን ዘንድ ትቀባዋለህ፤ ከፍልስጥኤማውያንም እጅ ሕዝቤን ያድናል።”