1 ሳሙኤል 14:50 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሳኦልም ሚስት ስም የአኪማኦስ ልጅ አኪናሆም ነበረች፤ የሠራዊቱም አለቃ ስም የሳኦል አጎት የኔር ልጅ አቤኔር ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሳኦል ሚስት አኪናሆም የምትባል የአኪማአስ ልጅ ነበረች፤ የሰራዊቱም አዛዥ አበኔር የሚባል የአጎቱ የኔር ልጅ ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሳኦል ሚስት አሒኖዓም የምትባል የአሒማዓጽ ልጅ ነበረች፤ የሠራዊቱም አዛዥ አበኔር የሚባል የሳኦል አጎት የኔር ልጅ ነበረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሚስቱም አሒኖዓም ተብላ የምትጠራ የአሒማዓጽ ልጅ ነበረች፤ የሠራዊቱም አዛዥ አበኔር ተብሎ የሚጠራው የአጐቱ የኔር ልጅ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሳኦልም ሚስት ስም የአኪማአስ ልጅ አኪናሆም ነበረ፥ የሠራዊቱም አለቃ ስም የሳኦል አጎት የኔር ልጅ አበኔር ነበረ። |
አበኔርም ወደ ኬብሮን በተመለሰ ጊዜ ኢዮአብ በበር ውስጥ በቈይታ ይናገረው ዘንድ ወደ አጠገቡ ወሰደው፤ በዚያም ለወንድሙ ለአሣሄል ደም ተበቅሎ ወገቡን መታው፤ ሞተም።
ነቢዩ ሳሙኤል፥ የቂስም ልጅ ሳኦል፥ የኔርም ልጅ አበኔር፥ የሶርህያም ልጅ ኢዮአብ የቀደሱት የእግዚአብሔር ንዋየ ቅድሳት ሁሉ ከሰሎሚትና ከወንድሞቹ እጅ በታች ነበረ።
በገለዓድ ምድር ባለው በምናሴ ነገድ እኩሌታ ላይ የዘብድያስ ልጅ ኢዮዳኢ፤ በብንያምም ልጆች ላይ የአበኔር ልጅ አሳሄል፤
ከቤተ ሰቡም አንዱ እርሱንና ብላቴናውን፥ “ወዴት ሄዳችሁ ኖሮአል?” አላቸው። እነርሱም፥ “አህዮችን ልንፈልግ ሄደን ነበር፤ ባጣናቸውም ጊዜ ወደ ሳሙኤል መጣን” አሉት።
ሳኦልም ዳዊትን ፍልስጥኤማዊውን ሊዋጋ ሲወጣ ባየ ጊዜ ለሠራዊቱ አለቃ ለአቤኔር፥ “አቤኔር ሆይ፥ ይህ ብላቴና የማን ልጅ ነው?” አለው። አቤኔርም፥ “ንጉሥ ሆይ፥ በሕያው ነፍስህ እምላለሁ አላውቅም” አለ።
ዳዊትም በቀስታ ተነሥቶ ሳኦል ወደ ሰፈረበት ቦታ መጣ፤ ሳኦልና የሠራዊቱ አለቃ የኔር ልጅ አቤኔርም የተኙበትን ስፍራ አየ፤ ሳኦልም በድንኳን ውስጥ ተኝቶ ነበር፤ ሕዝቡም በዙሪያው ሰፍሮ ነበር።