ፍልስጥኤማውያንም ሳኦልንና ልጆቹን በእግር በእግራቸው ተከትለው አባረሩአቸው፤ ፍልስጥኤማውያንም የሳኦልን ልጆች ዮናታንንና አሚናዳብን ሜልኪሳንም ገደሉ።
1 ሳሙኤል 14:49 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሳኦልም ወንዶች ልጆች ዮናታን፥ የሱዊ፥ ሚልኪሳ ነበሩ፤ የሁለቱም ሴቶች ልጆቹ ስም ይህ ነበረ፤ የታላቂቱ ስም ሜሮብ፥ የታናሺቱም ስም ሜልኮል ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሳኦል ወንዶች ልጆች ዮናታን፣ የሱዊ፣ ሜልኪሳ ነበሩ፤ ሴቶች ልጆቹም ትልቋ ሜሮብ፣ ትንሿ ሜልኮል ይባሉ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሳኦል ወንዶች ልጆች ዮናታን፥ ይሽዊና ማልኪሹዓ ነበሩ፤ ሴቶች ልጆቹም ትልቋ ሜሮብ፥ ትንሿ ሜልኮል ይባሉ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሳኦልም ወንዶች ልጆች ዮናታን፥ ይሽዊና ማልኪሹዓ ተብለው ይጠሩ ነበር፤ ታላቋ ሴት ልጁም ሜራብ ስትሆን፥ ታናሽዋ ሜልኮል ትባል ነበር፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሳኦልም ወንዶች ልጆች ዮናታን፥ የሱዊ፥ ሚልኪሳ ነበሩ፥ የሁለቱም ሴቶች ልጆቹ ስም ይህ ነበረ፥ የታላቂቱ ስም ሜሮብ፥ የታናሺቱም ስም ሜልኮል ነበረ። |
ፍልስጥኤማውያንም ሳኦልንና ልጆቹን በእግር በእግራቸው ተከትለው አባረሩአቸው፤ ፍልስጥኤማውያንም የሳኦልን ልጆች ዮናታንንና አሚናዳብን ሜልኪሳንም ገደሉ።
ዳዊትና ሰዎቹም ተነሥተው ሄዱ፤ ከፍልስጥኤማውያንም ሁለት መቶ ሰዎችን ገደሉ፤ ዳዊትም ለንጉሥ አማች ይሆን ዘንድ ሰለባቸውን አምጥቶ በቍጥራቸው ልክ ለንጉሡ ሰጠ። ሳኦልም ልጁን ሜልኮልን ዳረለት።
ፍልስጥኤማውያንም ሳኦልንና ልጆቹን ተከትለው አገኙአቸው። ፍልስጥኤማውያንም የሳኦልን ልጆች ዮናታንንና አሚናዳብን፥ ሜልኪሳንም ገደሉአቸው።