ሕዝቡም ሳኦልን፥ “በውኑ በእስራኤል ዘንድ ታላቅ መድኀኒት ያደረገ ዮናታን ዛሬ ይሞታልን? ይህ አይሁን፤ ዛሬ ለሕዝቡ ከእግዚአብሔር ጋር አድርጎአልና ሕያው እግዚአብሔርን! ከራሱ ጠጕር አንዲት በምድር ላይ አትወድቅም” አሉት። ሕዝቡም ያን ጊዜ ስለ ዮናታን ጸለዩ፤ እርሱም አልተገደለም።
1 ሳሙኤል 14:46 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሳኦልም ፍልስጥኤማውያንን ከመከተል ተመለሰ፤ ፍልስጥኤማውያንም ወደ ስፍራቸው ሄዱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሳኦል ፍልስጥኤማውያንን ከማሳደድ ተመለሰ፤ እነርሱም ወደ አገራቸው ተመለሱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሳኦል ፍልስጥኤማውያንን ከማሳደድ ተመለሰ፤ ፍልስጥኤማውያንም ወደ ስፍራቸው ተመለሱ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚያም በኋላ ሳኦል ፍልስጥኤማውያንን ከማሳደድ ተገታ፤ እነርሱም ተመልሰው ወደ አገራቸው ሄዱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሳኦልም ፍልስጥኤማውያንን ከመከተል ተመለሰ፥ ፍልስጥኤማውያንም ወደ ስፍራቸው ሄዱ። |
ሕዝቡም ሳኦልን፥ “በውኑ በእስራኤል ዘንድ ታላቅ መድኀኒት ያደረገ ዮናታን ዛሬ ይሞታልን? ይህ አይሁን፤ ዛሬ ለሕዝቡ ከእግዚአብሔር ጋር አድርጎአልና ሕያው እግዚአብሔርን! ከራሱ ጠጕር አንዲት በምድር ላይ አትወድቅም” አሉት። ሕዝቡም ያን ጊዜ ስለ ዮናታን ጸለዩ፤ እርሱም አልተገደለም።
ሳኦልም መንግሥቱን በእስራኤል ላይ አጸና፤ በዙሪያውም ካሉት ከጠላቶቹ ሁሉ ጋር፥ ከሞዓብም፥ ከአሞንም ልጆች፥ ከኤዶምያስም፥ ከቢዖርም፥ ከሱባም ነገሥታት፥ ከፍልስጥኤማውያንም ሁሉ ጋር ይዋጋ ነበር፤ በየሄደበትም ሁሉ ድል ይነሣ ነበር።
ፍልስጥኤማውያንም ጭፍሮቻቸውን ለጦርነት ሰበሰቡ፤ ራሳቸውም በይሁዳ በሰኮት ተሰበሰቡ፤ በሰኮትና በዓዜቃ መካከል በኤፌርሜም ሰፈሩ።