1 ሳሙኤል 14:40 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እስራኤልንም ሁሉ፥ “እናንተ አንድ ወገን ትሆናላችሁ፤ እኔና ልጄ ዮናታንም አንድ ወገን እንሆናለን” አለ። ሕዝቡም ሳኦልን፥ “ደስ የሚያሰኝህን አድርግ” አሉት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሳኦልም እስራኤላውያንን ሁሉ፣ “እናንተ በዚያ በኩል ቁሙ፤ እኔና ልጄ ዮናታን ደግሞ በዚህ በኩል እንቆማለን” አላቸው። ሰዎቹም፣ “መልካም መስሎ የታየህን አድርግ” ብለው መለሱለት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለእስራኤላውያን ሁሉ፥ “እናንተ በዚያ በኩል ቁሙ፤ እኔና ልጄ ዮናታን ደግሞ በዚህ በኩል እንቆማለን” አላቸው። ሰዎቹም፥ “መልካም መስሎ የታየህን አድርግ” አሉት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚያም በኋላ ሳኦል “እናንተ ሁላችሁም በዚያ በኩል ቁሙ፤ እኔና ልጄ ዮናታን ደግሞ በዚህ በኩል እንቆማለን” አላቸው። እነርሱም “መልካም መስሎ የታየህን አድርግ” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እስራኤልንም ሁሉ፦ እናንተ በአንድ ወገን ሁኑ፥ እኔና ልጄ ዮናታንም በሌላ ወገን እንሆናለን አለ። ሕዝቡም ሳኦልን ደስ የሚያሰኝህን አድርግ አሉት። |
ባልዋም ሕልቃና፥ “በዐይንሽ ደስ ያሰኘሽን አድርጊ፤ ጡትም እስኪተው ድረስ ተቀመጪ፤ ብቻ እግዚአብሔር ከአፍሽ የወጣውን ያጽና” አላት። ሴቲቱም ልጅዋን እያጠባች ጡት እስኪተው ድረስ ተቀመጠች።
ሳኦልም፥ “ፍልስጥኤማውያንን በሌሊት ተከትለን እንውረድ፤ እስኪነጋም ድረስ እንበዝብዛቸው፤ አንድ ሰው እንኳ አናስቀርላቸው” አለ። እነርሱም፥ “ደስ የሚያሰኝህን ሁሉ አድርግ” አሉት። ካህኑም፥ “ወደ እግዚአብሔር እንቅረብ” አለ።
እስራኤልን የሚያድን ሕያው እግዚአብሔርን! ኀጢኣቱ በልጄ በዮናታን ቢሆን ፈጽሞ ይሞታል” አለ። ከሕዝቡም ሁሉ አንድ የመለሰለት ሰው አልነበረም።
ሳኦልም እግዚአብሔርን፥ “የእስራኤል አምላክ ሆይ፥ ለእኔ ለባሪያህ ዛሬ ያልመለስህልኝ ስለ ምንድን ነው? ይህች በደል በእኔ፥ በልጄ በዮናታንም እንደ ሆነች አቤቱ የእስራኤል አምላክ ሆይ፥ ተናገር። ዕጣው ይህን የሚገልጥ ከሆነ ለሕዝብህ ለእስራኤል እውነትን ግለጥ፥” አለ። ዕጣም በዮናታንና በሳኦል ላይ ወጣ፤ ሕዝቡም ነፃ ወጣ።