1 ሳሙኤል 14:34 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሳኦልም፥ “በሕዝቡ መካከል እየዞራችሁ፦ እያንዳንዱ ሰው በሬውንና በጉን ወደ እኔ ያቅርብ፥ በዚህም እረዱና ብሉ፤ ከደሙም ጋር በመብላታችሁ እግዚአብሔርን አትበድሉ” በሉአቸው አለ። እያንዳንዱም ሰው ሁሉ በእጁ ያለውን በዚያች ሌሊት አቀረበ፤ በዚያም አረደው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም፣ “በሕዝቡ መካከል እየዞራችሁ፣ ‘እያንዳንዳችሁ በሬዎቻችሁንና በጎቻችሁን አምጡ፤ እዚሁ ዐርዳችሁ ብሉ፤ ነገር ግን ሥጋውን ከነደሙ በመብላት እግዚአብሔርን አትበድሉ’ በሏቸው” አለ። ስለዚህ በዚያች ሌሊት እያንዳንዱ ሰው በሬውን አምጥቶ በዚያ ዐረደው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሳኦልም፥ “በሕዝቡ መካከል እየዞራችሁ፥ ‘እያንዳንዳችሁ በሬዎቻችሁንና በጎቻችሁን አምጡ፤ እዚሁ ዐርዳችሁ ብሉ፤ ነገር ግን ሥጋውን ከነደሙ በመብላት ጌታን አትበድሉ’ በሏቸው” አለ። ስለዚህ በዚያች ሌሊት እያንዳንዱ ሰው በሬውን አምጥቶ በዚያ አረደው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህም በኋላ ሌላ ትእዛዝ እንዲህ ሲል አስተላለፈ፤ “ወደ ሕዝቡ ሄዳችሁ ‘የቀንድ ከብቶቻችሁንና በጎቻችሁን ሁሉ አምጡ፤ እነርሱንም ዐርዳችሁ በዚህ ስፍራ መመገብ አለባችሁ፤ ደም ያለበትንም እርጥብ ሥጋ በመብላት በእግዚአብሔር ፊት ኃጢአት አትሥሩ’ ብላችሁ ንገሩአቸው።” ስለዚህም ሕዝቡ ሁሉ በዚያን ሌሊት የቀንድ ከብቶቻቸውንና በጎቻቸውን ሁሉ አምጥተው በዚያ ዐረዱ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሳኦልም፦ በሕዝቡ መካከል እየዞራችሁ፦ እያንዳንዱ ሰው በሬውንና በጉን ወደ እኔ ያቅርብ፥ በዚህም እረዱና ብሉ፥ ከደሙም ጋር በመብላታችሁ እግዚአብሔርን አትበድሉ በሉአቸው አለ። እያንዳንዱም ሰው ሁሉ በእጁ ያለውን በሬውን በዚያች ሌሊት አቀረበ፥ በዚያም አረደው። |
ለሳኦልም፥ “እነሆ፥ ሕዝቡ ከደሙ ጋር በመብላታቸው እግዚአብሔርን በደሉ” ብለው ነገሩት። ሳኦልም በጌቴም “ትልቅ ድንጋይ አንከባልላችሁ አቅርቡልኝ” አላቸው።