ኤልያስም፥ “እግዚአብሔርን ትታችሁ በዓሊምን የተከተላችሁ፥ አንተና የአባትህ ቤት ናችሁ እንጂ እኔስ እስራኤልን አልገለባብጥም።
1 ሳሙኤል 14:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዮናታንም “አባቴ ምድሪቱን አስቸገረ፤ ከዚህ ማር ጥቂት ብቀምስ ዐይኔ እንደ በራ እዩ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዮናታንም እንዲህ አለ፤ “አባቴ በምድሪቱ ላይ ችግር ፈጥሯል፤ ከዚህ ማር ጥቂት በቀመስሁ ጊዜ ዐይኔ እንዴት እንደ በራ ተመልከቱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዮናታንም እንዲህ አለ፤ “አባቴ በምድሪቱ ላይ ችግር ፈጥሯል፤ ከዚህ ማር ጥቂት በቀመስሁ ጊዜ ዐይኔ እንዴት እንደ በራ ተመልከቱ! አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዮናታንም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “አባቴ በሕዝባችን ላይ የፈጠረው ችግር ምን ያኽል ከባድ ነው! ትንሽ ማር. አግኝቼ በመብላት ብርታት አግኝቼ ዐይኔ እንደ በራ ተመልከት! መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዮናታንም፦ አባቴ ምድሪቱን አስቸገረ፥ ከዚህ ማር ጥቂት ብቀምስ ዓይኔ እንደ በራ እዩ። |
ኤልያስም፥ “እግዚአብሔርን ትታችሁ በዓሊምን የተከተላችሁ፥ አንተና የአባትህ ቤት ናችሁ እንጂ እኔስ እስራኤልን አልገለባብጥም።
ኢያሱም፥ “ለምን አጠፋኸን? ዛሬ እንዳጠፋኸን እግዚአብሔር ዛሬ ያጥፋህ” አለው፤ እስራኤልም ሁሉ በድንጋይ ወገሩት፤ በእሳትም አቃጠሉት፤ በድንጋይም ወገሩአቸው።
ከሕዝቡም አንድ ሰው መልሶ፥ “አባትህ፦ ዛሬ መብል የሚበላ ሰው ርጉም ይሁን ብሎ ሕዝቡን መሐላ አምሎአቸዋል” አለው፤ ሕዝቡም ደከሙ።
ይልቅስ ሕዝቡ ካገኙት ከጠላቶቻቸው ምርኮ በልተው ቢሆን ኑሮ የፍልስጥኤማውያን መመታት ይበልጥ አልነበረምን?” አለ።