ኦርዮም ለዳዊት፥ “የእግዚአብሔር ታቦትና እስራኤል፥ ይሁዳም በድንኳን ተቀምጠዋል፤ ጌታዬ ኢዮአብና የጌታዬም አገልጋዮች በሰፊ ሜዳ ሰፍረዋል፤ እኔ ልበላና ልጠጣ ወይስ ከሚስቴ ጋር ልተኛ ወደ ቤቴ እሄዳለሁን? በሕይወትህና በሕያው ነፍስህ እምላለሁ! ይህን ነገር አላደርገውም” አለው።
1 ሳሙኤል 14:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያም ቀን አኪያ በእስራኤል ልጆች ፊት ኤፉድ ይለብስ ነበርና ሳኦል፥ “ኤፉድን አምጣ” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሳኦልም አኪያን፣ “የእግዚአብሔርን ታቦት ወደዚህ አምጣ” አለው፤ በዚያ ጊዜ ታቦቱ በእስራኤላውያን ዘንድ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሳኦልም አኪያን፥ “የእግዚአብሔርን ታቦት ወደዚህ አምጣ” አለው፤ በዚያን ጊዜ የእግዚአብሔር ታቦት በእስራኤላውያን ዘንድ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሳኦልም ካህኑን አኪያን “ኤፉዱን ይዘህ ና” አለው። በዚያን ቀን ካህኑ አኪያ ኤፉድ ለብሶ በእስራኤል ሕዝብ ፊት ነበር፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያም ቀን አኪያ በእስራኤል ልጆች ፊት ኤፉድ ለብሶ ነበርና ሳኦል፦ ኤፉድን አምጣ አለው። |
ኦርዮም ለዳዊት፥ “የእግዚአብሔር ታቦትና እስራኤል፥ ይሁዳም በድንኳን ተቀምጠዋል፤ ጌታዬ ኢዮአብና የጌታዬም አገልጋዮች በሰፊ ሜዳ ሰፍረዋል፤ እኔ ልበላና ልጠጣ ወይስ ከሚስቴ ጋር ልተኛ ወደ ቤቴ እሄዳለሁን? በሕይወትህና በሕያው ነፍስህ እምላለሁ! ይህን ነገር አላደርገውም” አለው።
በካህኑም በአልዓዛር ፊት ይቁም፤ እርሱም በእግዚአብሔር ፊት ፍርድ ይጠይቅለት፤ እርሱ ከእርሱም ጋር የእስራኤል ልጆች ማኅበር ሁሉ በቃሉ ይውጡ፤ በቃሉም ይግቡ።”
የእስራኤልም ልጆች ተነሥተው ወደ ቤቴል ወጡ፤ እግዚአብሔርንም፥ “የብንያምን ልጆች ለመውጋት መሪ ሆኖ ማን ይውጣልን?” ብለው ጠየቁት፤ እግዚአብሔርም፥ “ይሁዳ መሪ ይሁን” አለ፤
የእስራኤልም ልጆች ወጥተው በእግዚአብሔር ፊት እስከ ማታ ድረስ አለቀሱ፤ እግዚአብሔርንም፥ “ከወንድሞቻችን ከብንያም ልጆች ጋር ለመዋጋት ዳግመኛ እንቀርባለን?” ብለው ጠየቁ። እግዚአብሔርም “በእነርሱ ላይ ውጡ” አለ።
ሳኦልም ከእርሱ ጋር የነበሩትን ሕዝብ፥ “እስኪ ተቋጠሩ፤ ከእኛ ዘንድ የሄደ ማን እንደ ሆነ ተመልከቱ” አላቸው። በተቋጠሩም ጊዜ እነሆ፥ ዮናታንና ጋሻ ጃግሬው በዚያ አልተገኙም።
ሳኦልም፥ “ፍልስጥኤማውያንን በሌሊት ተከትለን እንውረድ፤ እስኪነጋም ድረስ እንበዝብዛቸው፤ አንድ ሰው እንኳ አናስቀርላቸው” አለ። እነርሱም፥ “ደስ የሚያሰኝህን ሁሉ አድርግ” አሉት። ካህኑም፥ “ወደ እግዚአብሔር እንቅረብ” አለ።
ዳዊትም ሳኦል በእርሱ ለክፋት ዝም እንደማይል ዐወቀ፤ ዳዊትም ካህኑን አብያታርን፥ “የእግዚአብሔርን ኤፉድ ወደዚህ አምጣ” አለው።
የቂርያትይዓሪም ሰዎችም መጥተው የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት አወጡ፤ በኮረብታውም ላይ ወዳለው ወደ አሚናዳብ ቤት አገቡአት፤ የእግዚአብሔርንም ታቦት እንዲጠብቅ ልጁን አልዓዛርን ቀደሱት።