1 ሳሙኤል 13:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሳኦልም ሳሙኤል እንደ ቀጠረው ጊዜ ሰባት ቀን ቈየ፤ ሳሙኤል ግን ወደ ጌልጌላ አልመጣም፤ ሕዝቡም ከእርሱ ተለይተው ተበታተኑ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም ሳሙኤል በሰጠው ቀጠሮ መሠረት ሰባት ቀን ጠበቀው። ነገር ግን ሳሙኤል ወደ ጌልገላ አልመጣም፤ የሳኦልም ሰራዊት መበታተን ጀመረ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም ሳሙኤል እንደ ቀጠረው ሰባት ቀን ጠበቀው። ነገር ግን ሳሙኤል ወደ ጌልገላ አልመጣም፤ የሳኦልም ሰዎች መበታተን ጀመሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲሁ ያደርግ ዘንድ ሳሙኤል ባዘዘው መሠረት፤ ሳኦል እስከ ሰባት ቀን ድረስ የሳሙኤልን መምጣት ሲጠብቅ ቈየ፤ ይሁን እንጂ እስከዚያ ጊዜ ድረስ ሳሙኤል ወደ ጌልጌላ አልመጣም ነበር፤ ከዚህም የተነሣ የሳኦል ሰዎች ሳኦልን በመክዳት ማፈግፈግ ጀመሩ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሳኦልም ሳሙኤል እንደ ቀጠረው ጊዜ ሰባት ቀን ቆየ፥ ሳሙኤል ግን ወደ ጌልገላ አልመጣም፥ ሕዝቡም ከእርሱ ተለይተው ተበታተኑ። |
በፊቴም ወደ ጌልገላ ትወርዳለህ፤ እኔም እነሆ፥ የሚቃጠለውን መሥዋዕት አቀርብ ዘንድ፥ የደኅንነትንም መሥዋዕት እሠዋ ዘንድ ወደ አንተ እወርዳለሁ፤ እኔ ወደ አንተ እስክመጣና የምታደርገውን እስከምነግርህ ድረስ ሰባት ቀን ትቈያለህ።”