ያንጊዜም ሳኦል ሦስት ሺህ ሰዎችን ከእስራኤል መረጠ፤ ሁለቱም ሺህ በማኪማስና በቤቴል ተራራ ከሳኦል ጋር ነበሩ፤ አንዱም ሺህ በብንያም ገባዖን ከልጁ ከዮናታን ጋር ነበሩ፤ የቀረውንም ሕዝብ እያንዳንዱን ወደ ድንኳኑ አሰናበተ።
1 ሳሙኤል 13:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሳሙኤልም ከጌልጌላ ተነሥቶ መንገዱን ሄደ፤ የቀሩትም ሕዝብ ሳኦልን ተከትለው ሰልፈኞቹን ሊገናኙ ሄዱ። ከጌልጌላም ተነሥተው ወደ ብንያም ገባዖን መጡ፤ ሳኦልም ከእርሱ ጋር የነበሩትን ሕዝብ ቈጠረ፤ ስድስት መቶም የሚያህሉ ሰዎች ነበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያ በኋላ ሳሙኤል ከጌልገላ ተነሥቶ በብንያም ግዛት ወዳለው ወደ ጊብዓ ወጣ። ሳኦልም ዐብረውት የነበሩትን ሰዎች ቈጠራቸው፤ ብዛታቸውም ስድስት መቶ ያህል ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያ ሳሙኤል ከጌልገላ ተነሥቶ በብንያም ግዛት ወዳለው ወደ ጊብዓ ሄደ። ሳኦልም አብረውት የነበሩትን ሰዎች ቆጠራቸው፤ ስድስት መቶ ያህል ነበሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሳሙኤልም ከጌልጌላ ተነሥቶ ሄደ፤ ሳኦልም ከወታደሮቹ ጋር ለመደባለቅ ሲሄድ የቀሩት ሰዎች ተከተሉት፤ ከጌልገላም ተነሥተው በብንያም ግዛት ወደምትገኘው ወደ ጊብዓ ሄዱ፤ ሳኦልም ሠራዊቱን በቈጠረ ጊዜ ብዛታቸው ስድስት መቶ ሆኖ ተገኘ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሳሙኤልም ከጌልገላ ተነሥቶ መንገዱን ሄደ፥ የቀሩትም ሕዝብ ሳኦልን ተከትለው ሰልፈኞቹን ሊገናኙ ሄዱ። ከጌልገላም ተነሥተው ወደ ብንያም ጊብዓ መጡ፥ ሳኦልም ከእርሱ ጋር የነበሩትን ሕዝብ ቆጠረ፥ ስድስት መቶም የሚያህሉ ሰዎች ነበሩ። |
ያንጊዜም ሳኦል ሦስት ሺህ ሰዎችን ከእስራኤል መረጠ፤ ሁለቱም ሺህ በማኪማስና በቤቴል ተራራ ከሳኦል ጋር ነበሩ፤ አንዱም ሺህ በብንያም ገባዖን ከልጁ ከዮናታን ጋር ነበሩ፤ የቀረውንም ሕዝብ እያንዳንዱን ወደ ድንኳኑ አሰናበተ።
ሳኦልም በመጌዶን ባለው በሮማኑ ዛፍ በታች በኮረብታው ላይ ተቀምጦ ነበር፤ ከእርሱም ጋር የነበረው ሕዝብ ስድስት መቶ የሚያህል ሰው ነበረ።
ሳሙኤልም እስራኤልን ለመገናኘት በጥዋት ገሥግሦ ሄደ። ለሳሙኤልም፥ “ሳኦል ወደ ቀርሜሎስ መጣ፤ እነሆም፥ ለራሱ የመታሰቢያ ዐምድ አቆመ” ብለው ነገሩት። ሳሙኤልም ሰረገላውን መልሶ ወደ ጌልጌላ ወደ ሳኦል ወረደ፤ ከአማሌቅ ዘንድ ከአመጣውም ከአማረው ከምርኮው መንጋ ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መሥዋዕት ሲሠዋ አገኘው፤