በሕዝቤ በእስራኤል ላይ ፈራጆችን በሾምሁ ጊዜ ከጠላቶችህ ሁሉ አሳርፍሃለሁ። እግዚአብሔርም ደግሞ፦ ቤት እንደምትሠራለት ይነግርሃል፤ እሠራለታለሁ ብለሃልና።
1 ሳሙኤል 12:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አምላካቸውንም እግዚአብሔርን ረሱ፤ ለአሶር ሠራዊትም አለቃ ለሲሣራ እጅ፥ ለፍልስጥኤማውያንም እጅ፥ ለሞዓብም ንጉሥ እጅ አሳልፎ ሰጣቸው፤ እነርሱም ወጉአቸው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እነርሱ ግን አምላካቸውን እግዚአብሔርን ረሱት፤ ስለዚህ ለአሦር የጦር አዛዥ ለሲሣራ፣ ለፍልስጥኤማውያንና ለሞዓብ ንጉሥ አሳልፎ ሸጣቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱ ግን አምላካቸውን ጌታን ረሱት፤ ስለዚህ ለሓጾር የጦር አዛዥ ለሲሣራ፥ ለፍልስጥኤማውያንና ለሞዓብ ንጉሥ አሳልፎ ሰጣቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን ሕዝቡ አምላካቸውን እግዚአብሔርን ረሱ፤ ስለዚህ እግዚአብሔር የሓጾር ሠራዊት አዛዥ ለነበረው ለሲሣራ፥ ለፍልስጥኤማውያን፥ ለሞአብም ንጉሥ አሳልፎ ሰጣቸው፤ እነርሱም እስራኤላውያንን ድል ነሡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አምላካቸውንም እግዚአብሔርን ረሱ፥ ለአሶር ሠራዊትም አለቃ ለሲሣራ እጅ፥ ለፍልስጥኤማውያንም እጅ፥ ለሞዓብም ንጉሥ እጅ አሳልፎ ሰጣቸው፥ ከእነርሱም ጋር ተዋጉ። |
በሕዝቤ በእስራኤል ላይ ፈራጆችን በሾምሁ ጊዜ ከጠላቶችህ ሁሉ አሳርፍሃለሁ። እግዚአብሔርም ደግሞ፦ ቤት እንደምትሠራለት ይነግርሃል፤ እሠራለታለሁ ብለሃልና።
አንዱ ሽሁን እንዴት ያሳድዳቸዋል? ሁለቱስ ዐሥሩን ሽህ እንዴት ያባርሩአቸዋል? እግዚአብሔር ፍዳውን አምጥቶባቸዋልና። አምላካችንም አሳልፎ ሰጥቶአቸዋልና።
የእስራኤልም ልጆች በእግዚአብሔር ፊት እንደ ገና ክፉ ሥራ ሠሩ፤ እግዚአብሔርም በፍልስጥኤማውያን እጅ አርባ ዓመት አሳልፎ ሰጣቸው።
እግዚአብሔርም በእስራኤል ላይ ተቈጣ፤ ወደ ማረኳቸውም ማራኪዎች እጅ አሳልፎ ሰጣቸው፤ ማረኩአቸውም፤ በዙሪያቸውም ባሉት በጠላቶቻቸው እጅ አሳልፎ ሰጣቸው፤ ከዚያም ወዲያ ጠላቶቻቸውን ሊቋቋሙ አልቻሉም።
የእስራኤልም ልጆች በእግዚአብሔር ፊት እንደ ገና ክፉ ሥራ ሠሩ፤ በእግዚአብሔርም ፊት ክፉ ስለ ሠሩ እግዚአብሔር የሞዓብን ንጉሥ ዔግሎምን በእስራኤል ላይ አበረታባቸው።
ከእርሱም በኋላ የሐናት ልጅ ሴሜጋር ተነሣ፤ ከፍልስጥኤማውያንም ስድስት መቶ ሰው በበሬ መውጊያ ገደለ፤ እርሱም ደግሞ እስራኤልን አዳነ።
እግዚአብሔርም በአሦር በነገሠው በከነዓን ንጉሥ በኢያቢን እጅ አሳልፎ ሰጣቸው፤ የሠራዊቱም አለቃ ሲሣራ ነበረ፤ እርሱም በአሕዛብ አሪሶት ይቀመጥ ነበረ።
ነገር ግን የእግዚአብሔርን ቃል ባትሰሙ፥ በእግዚአብሔርም ትእዛዝ ላይ ብታምፁ፥ በእናንተና በንጉሣችሁ ላይ የእግዚአብሔር እጅ ትመጣለች።