ሙሴም ለሕዝቡ፥ “አትፍሩ፤ ዛሬ የምታዩአቸውን ግብፃውያንን ለዘለዓለም አታዩአቸውምና ቁሙ፤ ዛሬ ለእናንተ የሚያደርጋትን የእግዚአብሔርን ማዳን እዩ።
1 ሳሙኤል 12:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሁንም ቁሙ፤ እግዚአብሔርም በዐይናችሁ ፊት የሚያደርገውን ይህን ታላቅ ነገር ተመልከቱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ስለዚህ ጸንታችሁ ቁሙ፤ እግዚአብሔር በዐይናችሁ ፊት የሚያደርገውንም ይህን ታላቅ ነገር ተመልከቱ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ ጸንታችሁ ቁሙ፤ ጌታ በዐይናችሁ ፊት የሚያደርገውንም ይህን ታላቅ ነገር ተመልከቱ! አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ባላችሁበት ጸንታችሁ ቁሙ፤ እግዚአብሔር በፊታችሁ የሚያደርገውንም ድንቅ ነገር ታያላችሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሁንም ቁሙ፥ እግዚአብሔርም በዓይናችሁ ፊት ወደሚያደርገው ወደዚህ ታላቅ ነገር ተመልከቱ። |
ሙሴም ለሕዝቡ፥ “አትፍሩ፤ ዛሬ የምታዩአቸውን ግብፃውያንን ለዘለዓለም አታዩአቸውምና ቁሙ፤ ዛሬ ለእናንተ የሚያደርጋትን የእግዚአብሔርን ማዳን እዩ።
እስራኤልም እግዚአብሔር በግብፃውያን ላይ ያደረጋትን ታላቂቱን እጅ አዩ፤ ሕዝቡም እግዚአብሔርን ፈሩ፤ በእግዚአብሔርም አመኑ፤ ባሪያውንም ሙሴን አከበሩ።
አሁንም ቁሙ፤ በእግዚአብሔርም ፊት እፋረዳችኋለሁ፤ ለእናንተና ለአባቶቻችሁ ያደረገውን የእግዚአብሔርን ጽድቅ ሁሉ እነግራችኋለሁ።