ንጉሡም ተመልሶ እስከ ዮርዳኖስ ድረስ መጣ። የይሁዳ ሰዎችም ንጉሡን ሊቀበሉ፥ ንጉሡንም ዮርዳኖስን ሊያሻግሩ ወደ ጌልገላ መጡ።
1 ሳሙኤል 11:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሳሙኤልም ሕዝቡን፥ “ኑ፤ ወደ ጌልገላ እንሂድ፤ በዚያም መንግሥቱን እናጽና” አላቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ሳሙኤል ሕዝቡን፣ “ኑና ወደ ጌልገላ እንሂድ፤ ንግሥናውን እናጽና” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም ሳሙኤል ሕዝቡን፥ “ኑና ወደ ጌልገላ እንሂድ፤ ንግሥናውንም እናጽና” አለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሳሙኤልም “ሁላችንም ወደ ጌልጌላ እንሂድና ሳኦል ንጉሣችን መሆኑን እንደገና በይፋ እናረጋግጥ” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሳሙኤልም ሕዝቡን፦ ኑ፥ ወደ ጌልገላ እንሂድ፥ በዚያም መንግሥቱን እናድስ አላቸው። |
ንጉሡም ተመልሶ እስከ ዮርዳኖስ ድረስ መጣ። የይሁዳ ሰዎችም ንጉሡን ሊቀበሉ፥ ንጉሡንም ዮርዳኖስን ሊያሻግሩ ወደ ጌልገላ መጡ።
ነገር ግን ጌልገላ ፈጽሞ ትማረካለችና፥ ቤቴልም እንዳልነበረች ትሆናለችና ቤቴልን አትፈልጉ፤ ወደ ጌልገላም አትሂዱ፤ ወደ ቤርሳቤህም አትለፉ።”
በፊቴም ወደ ጌልገላ ትወርዳለህ፤ እኔም እነሆ፥ የሚቃጠለውን መሥዋዕት አቀርብ ዘንድ፥ የደኅንነትንም መሥዋዕት እሠዋ ዘንድ ወደ አንተ እወርዳለሁ፤ እኔ ወደ አንተ እስክመጣና የምታደርገውን እስከምነግርህ ድረስ ሰባት ቀን ትቈያለህ።”
በነጋውም የአዛጦን ሰዎች ማለዱ፤ ወደ ዳጎንም ቤት ገቡ፤ እነሆም፥ ዳጎን በእግዚአብሔር ታቦት ፊት በምድር ላይ በግንባሩ ወድቆ አገኙት፤ ዳጎንንም አንሥተው በስፍራው አቆሙት።
በየዓመቱም ወደ ቤቴል፥ ወደ ጌልጌላና ወደ መሴፋ ይዞር ነበር፤ በእነዚያም በተቀደሱ ስፍራዎች ሁሉ በእስራኤል ላይ ይፈርድ ነበር።