አዳምንም አስወጣው፤ ደስታ በሚገኝባት በገነት አንጻርም አኖረው፤ ወደ ሕይወት ዛፍ የሚወስደውንም መንገድ ለመጠበቅ የምትገለባበጥ የነበልባል ሰይፍን በእጃቸው የያዙ ኪሩቤልን አዘዛቸው።
1 ሳሙኤል 10:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም ሮጦ ከዚያ አመጣው፤ እርሱም በሕዝቡ መካከል አቆመው፤ ከሕዝቡም ሁሉ ይልቅ ረዥም ነበረ፤ ሕዝቡም ከትከሻው በታች ሆኑ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነርሱም ሮጠው ከተደበቀበት አመጡት፤ በሕዝቡ መካከል በቆመ ጊዜም ቁመቱ ከሌሎቹ ሁሉ ይልቅ ከትከሻው በላይ ዘለግ ያለ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱም ሮጠው ከተደበቀበት አመጡት፤ በሕዝቡ መካከል በቆመ ጊዜም ቁመቱ ከሌሎቹ ሁሉ ይልቅ ከትከሻው በላይ ዘለግ ያለ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህም እነርሱ ፈጠን ብለው በመሄድ ከተሸሸገበት አውጥተው ወደ ሕዝቡ አመጡት፤ ሕዝቡም ሳኦል በትከሻውና በቁመት ከሁሉ የሚበልጥ መሆኑን ተመለከቱ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነርሱም ሮጠው ከዚያ አመጡት፥ እርሱም በሕዝቡ መካከል ቆመ፥ ከሕዝቡም ሁሉ ይልቅ ከትከሻው ወደ ላይ ከፍ ያለ ቁመተ ረጅም ነበረ። |
አዳምንም አስወጣው፤ ደስታ በሚገኝባት በገነት አንጻርም አኖረው፤ ወደ ሕይወት ዛፍ የሚወስደውንም መንገድ ለመጠበቅ የምትገለባበጥ የነበልባል ሰይፍን በእጃቸው የያዙ ኪሩቤልን አዘዛቸው።
እግዚአብሔር ግን ሳሙኤልን፥ “ፊቱን፥ የቁመቱንም ዘለግታ አትይ፤ ሰው እንደሚያይ እግዚአብሔር አያይምና ናቅሁት፤ ሰው ፊትን ያያል፤ እግዚአብሔር ግን ልብን ያያል” አለው።
ከብንያም ልጆች ስሙ ቂስ የተባለ አንድ ሰው ነበረ፥ እርሱም የአብሔል ልጅ፥ የያሬድ ልጅ፥ የባሔር ልጅ፥ የብንያም ሰው፥ የአፌቅ ልጅ፥ ጽኑዕ ኀያል ሰው ነበረ።
ለእርሱም ሳኦል የሚባል የተመረጠ መልካም ልጅ ነበረው፤ በምድር ሁሉ ላይ ከእስራኤል ልጆች ከእርሱ ይልቅ መልካም የሆነ ሰው አልነበረም፤ ከሕዝቡም ሁሉ ይልቅ ከትከሻውና ከዚያም በላይ ቁመቱ ዘለግ ያለ ነበረ።