በእነርሱ እጠራ ዘንድ፥ አምላክም እሆናቸው ዘንድ ከግብፅ ምድር ያወጣኋቸው አምላካቸው እግዚአብሔር እኔ እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።
1 ሳሙኤል 10:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእስራኤልንም ልጆች፥ “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ‘እስራኤልን ከግብፅ አወጣሁ፤ ከግብፅ ንጉሥ ከፈርዖንም እጅ፥ ከሚያስጨንቁአችሁም ነገሥታት ሁሉ እጅ አዳንኋችሁ’ አላቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲህ አላቸው፤ “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘እስራኤልን ከግብጽ አወጣሁት፤ ከግብጻውያን እጅ ይጨቍኗችሁ ከነበሩት ከሌሎቹ መንግሥታት ሁሉ እጅ ታደግኋችሁ።’ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲህ አላቸው፤ “የእስራኤል አምላክ ጌታ እንዲህ ይላል፤ ‘እስራኤልን ከግብጽ አወጣሁት፤ ከግብፃውያን እጅ ይጨቁኗችሁ ከነበሩት ከሌሎቹ መንግሥታት ሁሉ እጅ ታደግኋችሁ።’ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲህም አላቸው፦ “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር፦ ‘እናንተን እስራኤልን ከግብጽ አወጣኋችሁ፤ ከግብጽ ኀይልና ከሚጨቊኑአችሁ መንግሥታት ሁሉ ጭቈና አዳንኳችሁ’ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእስራኤልንም ልጆች የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እስራኤልን ከግብጽ አወጣሁ፥ ከግብጻውያንም እጅ ከሚያስጨንቁአችሁም ነገሥታት ሁሉ እጅ አዳንኋችሁ። |
በእነርሱ እጠራ ዘንድ፥ አምላክም እሆናቸው ዘንድ ከግብፅ ምድር ያወጣኋቸው አምላካቸው እግዚአብሔር እኔ እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።
በሚገፋችሁም ጠላት ላይ በምድራችሁ ወደ ሰልፍ ስትወጡ በምልክት መለከቶችን ንፉ፤ በእግዚአብሔርም በአምላካችሁ ፊት ትታሰባላችሁ፤ ከጠላቶቻችሁም ትድናላችሁ።
የእግዚአብሔርም መልአክ ከገልገላ ወደ ቀላውትምኖስ ወደ ቤቴል ወደ እስራኤል ቤት ወጥቶ እንዲህ አላቸው፥ “እግዚአብሔር እኔ ከግብፅ አውጥቼአችኋለሁ፤ እሰጣችሁም ዘንድ ለአባቶቻችሁ ወደ ማልሁላቸው ምድር አግብቻችኋለሁ፤ እኔም፦ ከእናንተ ጋር ያደረግሁትን ቃል ኪዳን ለዘለዓለም አላፈርስም፤
ያዕቆብና ልጆቹ ወደ ግብጽ በገቡ ጊዜ ግብጻውያን አስጨነቁአቸው፤ አባቶቻችሁም ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፤ እግዚአብሔርም ሙሴንና አሮንን ላከ፤ አባቶቻችሁንም ከግብጽ አውጥተው በዚህ ቦታ አኖሩአቸው።