እርሱ ግን፦ ወደ እርስዋ ተመለከተና እንዲህ አላት፥ “አንቺ ከሰነፎች ሴቶች እንደ አንዲቱ ተናገርሽ፤ ከእግዚአብሔር እጅ መልካሙን ተቀበልን፥ ክፉውን ነገርስ አንታገሥምን?” በዚህ በደረሰበት ሁሉ ኢዮብ በእግዚአብሔር ፊት በከንፈሩ አልበደለም።
1 ጴጥሮስ 2:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በጎ እያደረጋችሁ፥ የማያውቁትን ሞኞች ዝም ታሰኙ ዘንድ እንዲህ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነውና፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምክንያቱም፣ መልካም በማድረግ የአላዋቂዎችን ከንቱ ንግግር ዝም እንድታሰኙ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚህ መንገድ መልካም በማድረግ የሞኞችን አላዋቂነት ዝም እንድታሰኙ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መልካም በማድረግ የሞኞችን አላዋቂ ንግግር ዝም እንድታሰኙ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በጎ እያደረጋችሁ፥ የማያውቁትን ሞኞች ዝም ታሰኙ ዘንድ እንዲህ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነውና፤ |
እርሱ ግን፦ ወደ እርስዋ ተመለከተና እንዲህ አላት፥ “አንቺ ከሰነፎች ሴቶች እንደ አንዲቱ ተናገርሽ፤ ከእግዚአብሔር እጅ መልካሙን ተቀበልን፥ ክፉውን ነገርስ አንታገሥምን?” በዚህ በደረሰበት ሁሉ ኢዮብ በእግዚአብሔር ፊት በከንፈሩ አልበደለም።
የሕዝቤ አለቆች አላወቁኝም፤ እነርሱ ሰነፎች ልጆች ናቸው፤ ማስተዋልም የላቸውም፤ ክፉ ነገርን ለማድረግ ብልሃተኞች ናቸው፤ በጎ ነገርን ማድረግ ግን አያውቁም።
እግዚአብሔርን ሲያውቁት እንደ እግዚአብሔርነቱ አላከበሩትም፤ አላመሰገኑትምም፤ ነገር ግን ካዱት፤ በአሳባቸውም ረከሱ፤ ልቡናቸውም ባለማወቅ ጨለመ።
እናንተ ሰነፎች የገላትያ ሰዎች ሆይ፥ ለዐይን በሚታየው እውነት እንዳታምኑ ማን አታለላችሁ? እርሱም እንዲሰቀል አስቀድሞ የተጻፈለት ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።
ደንቆሮ፥ ብልሃተኛም ያልሆንህ ሕዝብ ሆይ፥ ለእግዚአብሔር ይህን ትመልሳለህን? የፈጠረህ አባትህ አይደለምን? የፈጠረህና ያጸናህ እርሱ ነው።
እኛ ደግሞ አስቀድመን የማናስተውል ነበርንና፤ የማንታዘዝ፥ የምንስት፥ ለምኞትና ለልዩ ልዩ ተድላ እንደ ባሪያዎች የምንገዛ፥ በክፋትና በምቀኝነት የምንኖር፥ የምንጣላ፥ እርስ በርሳችን የምንጠላላ ነበርን።
ስለሚመለከቱት ስለ መልካም ሥራችሁ፥ ክፉ እንደምታደርጉ በዚያ እናንተን በሚያሙበት ነገር፥ በሚጎበኝበት ቀን እግዚአብሔርን ያከብሩት ዘንድ በአሕዛብ መካከል ኑሮአችሁ መልካም ይሁን።
እነዚህ ግን ለመጠመድና ለመጥፋት በፍጥረታቸው እንደ ተወለዱ አእምሮ እንደ ሌላቸው እንስሶች ሆነው፥ በማያውቁት ነገር እየተሳደቡ በጥፋታቸው ይጠፋሉ፤