1 ነገሥት 9:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም አለው፥ “ወንድሜ ሆይ! የሰጠኸኝ እነዚህ ከተሞች ምንድን ናቸው?” እስከ ዛሬም ድረስ ወሰን ብሎ ጠራቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም፣ “ወንድሜ ሆይ፤ እነዚህ የሰጠኸኝ ከተሞች ምንድን ናቸው?” አለ፤ እነዚህንም “ከቡል ምድር” አላቸው፤ እስከ ዛሬም በዚሁ ስም ይጠራሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰሎሞንን “ወንድሜ ሆይ! የሰጠኸኝ ከተሞች ለካ እነዚህ ናቸውን?” አለው፤ በዚህ ምክንያት እስከ ዛሬ ድረስ ያ አካባቢ በሙሉ ካቡል እየተባለ ይጠራል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰሎሞንን “ወንድሜ ሆይ! የሰጠኸኝ ከተሞች ለካ እነዚህ ናቸውን?” አለው፤ በዚህ ምክንያት እስከ ዛሬ ድረስ ያ አካባቢ በሙሉ ካቡል እየተባለ ይጠራል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም “ወንድሜ ሆይ! የሰጠኸኝ እነዚህ ከተሞች ምንድር ናቸው?” አለ። እስከ ዛሬም ድረስ የከቡል አገር ተብለው ተጠሩ። |
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “የሰሎሞን ምርኮኞችን በኤዶምያስ ዘግተዋልና፥ የወንድሞችንም ቃል ኪዳን አላሰቡምና ስለ ሦስት ወይም ስለ አራት የጢሮስ ኀጢአት አልመለስላቸውም።
ወደ ፀሐይ መውጫ ወደ ቤቴጌነት ይዞራል፤ በመስዕም በኩል ከዛብሎንና ከጋይ ከይፍታሕኤል ይያያዛል ወደ ሳፍቱ ቤታሜሕና ወደ ኢንሂል ይደርሳል፤ ወደ ኮባ ማሾሜልም ያልፋል፤