1 ነገሥት 7:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በአዕማዱም ራስ ላይ የሱፍ አበባ የሚመስል ሥራ አደረገ። እንዲሁም የአዕማዱ ሥራ ተጨረሰ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዐናቱ ላይ ያሉት ጕልላቶች የሱፍ አበባ ቅርጽ ነበራቸው። የምሰሶዎቹም ሥራ በዚህ ሁኔታ ተፈጸመ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በምሰሶዎቹ ጫፍ ላይ የአሸንድዬ አበባ የሚመስሉ ከነሐስ የተሠሩ ጉልላቶች ነበሩ። የምሰሶዎቹም ሥራ በዚህ ዓይነት ተፈጸመ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በምሰሶዎቹ ጫፍ ላይ የአሸንድዬ አበባ የሚመስሉ ከነሐስ የተሠሩ ጉልላቶች ነበሩ። የምሰሶዎቹም ሥራ በዚህ ዐይነት ተፈጸመ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በአዕማዱም ራስ ላይ የሱፍ አበባ የሚመስል ሥራ ነበር፤ እንዲሁም የአዕማዱ ሥራ ተጨረሰ። |
አዕማዱንም በመቅደሱ ወለል አጠገብ አቆማቸው፤ የቀኙንም ዓምድ አቁሞ ያቁም ብሎ ጠራው፤ የግራውንም ዓምድ አቁሞ በለዝ ብሎ ጠራው።
ሁለቱንም አዕማድ፥ በሁለቱም አዕማድ ራስ ላይ የነበሩትን ኩብ የሚመስሉትን ጕልላቶች፥ በሁለቱም አዕማድ ላይ የነበሩትን ሁለቱን ጕልላቶች የሚሸፍኑትን ሁለቱን መርበቦች፥