La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ነገሥት 7:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በሁ​ለ​ቱም አዕ​ማድ ራስ ላይ እን​ዲ​ቀ​መጡ ከፈ​ሰሰ ናስ ሁለት ጕል​ላ​ትን ሠራ፤ የአ​ን​ዱም ጕል​ላት ቁመት አም​ስት ክንድ፥ የሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ጕል​ላት ቁመት አም​ስት ክንድ ነበረ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እንዲሁም በምሰሶዎቹ ዐናት ላይ የሚሆኑ፣ ሁለት ጕልላት ከቀለጠ ናስ ሠራ፤ የእያንዳንዱም ጕልላት ቁመት ዐምስት ክንድ ነበር።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እንዲሁም በምሰሶዎቹ ላይ የሚቆሙ የእያንዳንዳቸው ቁመት ሁለት ሜትር ከኻያ ሳንቲ ሜትር የሆነ ሁለት የነሐስ ጉልላቶችን ሠራ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እንዲሁም በምሰሶዎቹ ላይ የሚቆሙ የእያንዳንዳቸው ቁመት ሁለት ሜትር ከኻያ ሳንቲ ሜትር የሆነ ሁለት የነሐስ ጒልላቶችን ሠራ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በሁለቱም አዕማድ ራስ ላይ እንዲቀመጡ ከፈሰሰ ናስ ሁለት ጕልላት ሠራ፤ የአንዱም ጕልላት ቁመት አምስት ክንድ፥ የሁለተኛውም ጕልላት ቁመት አምስት ክንድ ነበረ።

Ver Capítulo



1 ነገሥት 7:16
8 Referencias Cruzadas  

በቤቱ ውስጥ ላለው ወለል ሁለ​ቱን የናስ አዕ​ማድ ሠራ፤ የአ​ን​ዱም ዓምድ ቁመት ዐሥራ ስም​ንት ክንድ ነበረ፤ የዙ​ሪ​ያ​ውም መጠን ዐሥራ ሁለት ክንድ ነበረ፤ የዓ​ም​ዱም ውፍ​ረት አንድ ጋት ነበረ፤ ውስጠ ክፍ​ትም ነበረ። ሁለ​ተ​ኛ​ውም ዓምድ እን​ዲሁ ነበረ።


በአ​ዕ​ማ​ዱም ራስ ላይ የነ​በ​ሩ​ትን ጕል​ላ​ቶች ይሸ​ፍኑ ዘንድ ሁለት እንደ መር​በብ ሥራ አደ​ረገ፤ አን​ዱም መር​በብ ለአ​ንዱ ጕል​ላት፥ ሁለ​ተ​ኛ​ውም መር​በብ ለሁ​ለ​ተ​ኛው ጕል​ላት ነበረ።


አም​ስ​ቱ​ንም ምሰ​ሶ​ዎች፥ ኵላ​ቦ​ቻ​ቸ​ው​ንም አደ​ረጉ፤ ጉል​ላ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንና ዘን​ጎ​ቻ​ቸ​ው​ንም በወ​ርቅ ለበ​ጡ​አ​ቸው፤ አም​ስ​ቱም እግ​ሮ​ቻ​ቸው የናስ ነበሩ።


የም​ሰ​ሶ​ዎ​ቹም እግ​ሮች የናስ፥ የም​ሰ​ሶ​ዎ​ቹም ኵላ​ቦ​ችና ዘን​ጎች የብር ነበሩ፤ የም​ሰ​ሶ​ዎ​ቹም ጕል​ላ​ቶች በብር ተለ​ብ​ጠው ነበር፤ በአ​ደ​ባ​ባዩ ላሉ ምሰ​ሶ​ዎች ሁሉ የብር ዘን​ጎች ነበ​ሩ​አ​ቸው።


ከናስ የተ​ሠሩ ምሰ​ሶ​ዎ​ቹም አራት፥ እግ​ሮ​ቹም አራት ነበሩ፤ ኵላ​ቦ​ቹም የብር ነበሩ፤ ጕል​ላ​ቶ​ቹና ዘን​ጎ​ቹም በብር ተለ​ብ​ጠው ነበር።


ከሺህ ሰባት መቶ ሰባ አም​ስት ሰቅል የም​ሰ​ሶ​ዎ​ቹን ኵላ​ቦ​ችና ዘን​ጎች አደ​ረገ፤ የም​ሰ​ሶ​ዎ​ቹ​ንም ጕል​ላ​ቶች ለበጠ።


የና​ሱም ጕል​ላት በላዩ ነበረ፤ የአ​ን​ዱም ጕል​ላት ቁመት አም​ስት ክንድ ነበረ፤ በጕ​ል​ላ​ቱም ላይ በዙ​ሪ​ያው ሁሉ ከናስ የተ​ሠሩ መር​በ​ብና ሮማ​ኖች ነበ​ሩ​በት፤ በሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ዐምድ ደግሞ እን​ደ​ዚህ ያለ ነገ​ርና ሮማ​ኖች ነበ​ሩ​በት።