1 ነገሥት 5:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሰሎሞንና የኪራም አናጢዎች፥ ጌባላውያንም ወቀሩአቸው፤ ለመሠረትም አኖሩአቸው፤ ቤቱንም ለመሥራት እንጨቱንና ድንጋዮቹን ሦስት ዓመት አዘጋጁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሰሎሞንና የኪራም የእጅ ባለሙያዎች እንዲሁም የጌባል ሰዎች ለቤተ መቅደሱ የሚያስፈልገውን ዕንጨትና ድንጋይ ፈልጠው አዘጋጁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሰሎሞንና የኪራም ጥበበኞች ሠራተኞችና እንዲሁም የቢብሎስ ሰዎች ቤተ መቅደሱን ለመሥራት የሚያስችላቸውን ድንጋይና እንጨት ሁሉ አዘጋጁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሰሎሞንና የኪራም ጥበበኞች ሠራተኞችና እንዲሁም የቢብሎስ ሰዎች ቤተ መቅደሱን ለመሥራት የሚያስችላቸውን ድንጋይና እንጨት ሁሉ አዘጋጁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሰሎሞንና የኪራምም አናጢዎች ጌባላውያንም ወቀሩአቸው፤ ቤቱንም ለመሥራት እንጨቱንና ድንጋዮቹን አዘጋጁ። |
ዳዊትም በእስራኤል ምድር የነበሩትን መጻተኞች ይሰበስቡ ዘንድ አዘዘ፤ የእግዚአብሔርንም ቤት ለመሥራት የሚወቀሩትን ድንጋዮች ይወቅሩ ዘንድ ጠራቢዎችን አኖረ።
በአንቺ ውስጥ የነበሩ የጌባል ሽማግሌዎችና ጥበበኞችዋ ስብራትሽን ይጠግኑ ነበር፤ ከአንቺም ጋር ይነግዱ ዘንድ የባሕር መርከቦች ሁሉና መርከበኞቻቸው በመካከልሽ ነበሩ።
በፍልስጥኤም ያለው የጌባላውያን ምድር ሁሉ፥ በምሥራቅም በኩል ከአርሞንዔም ተራራ በታች ካለችው ጌልገላ ጀምሮ እስከ ኤማት መግቢያ ድረስ ያለችው ሊባኖስ ሁሉ፥