ስለ ዛፍም ከሊባኖስ ዝግባ ጀምሮ በቅጥር ግንብ ላይ እስከሚበቅለው እስከ አሽክት ድረስ ይናገር ነበር፤ ደግሞም ስለ አውሬዎችና ስለ ወፎች ስለ ተንቀሳቃሾችና ስለ ዓሣዎች ይናገር ነበር።
1 ነገሥት 4:32 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰሎሞንም ሦስት ሺህ ምሳሌዎችን ተናገረ፤ መሐልዩም አንድ ሺህ አምስት ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም ሦስት ሺሕ ምሳሌዎችን ተናገረ፤ የመሓልዩም ቍጥር ሺሕ ዐምስት ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሦስት ሺህ ምሳሌዎችንና አንድ ሺህ አምስት የመዝሙር ድርሰቶችን ደረሰ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሦስት ሺህ ምሳሌዎችንና አንድ ሺህ አምስት የመዝሙር ድርሰቶችን ደረሰ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም ሦስት ሺህ ምሳሌዎች ተናገረ፤ መኃልዩም ሺህ አምስት ነበረ። |
ስለ ዛፍም ከሊባኖስ ዝግባ ጀምሮ በቅጥር ግንብ ላይ እስከሚበቅለው እስከ አሽክት ድረስ ይናገር ነበር፤ ደግሞም ስለ አውሬዎችና ስለ ወፎች ስለ ተንቀሳቃሾችና ስለ ዓሣዎች ይናገር ነበር።
ከዚህም ሁሉ በላይ፥ ልጄ ሆይ፥ ተግሣጽን ስማ፥ ፍጻሜ የሌላቸው ብዙ መጻሕፍትን አታድርግ። እጅግም ምርምር ሰውነትን ያደክማል።