“ከቄድሞትም ምድረ በዳ የሰላምን ቃል ይነግሩት ዘንድ ወደ ሐሴቦን ንጉሥ ወደ ሴዎን እንዲህ ብዬ መልእክተኞችን ላክሁ፦
1 ነገሥት 4:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በአሞራውያን ንጉሥ በሴዎንና በባሳን ንጉሥ በዐግ ሀገር፥ በጋድ ሀገር፥ የአዴ ልጅ ጌቤር ነበረ፤ በይሁዳም ምድር ላይ እርሱ ብቻውን ሹም ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የኡሪ ልጅ ጌበር፣ በገለዓድ፤ በአሞራውያን ንጉሥ በሴዎን ምድር፣ በባሳን ንጉሥ በዐግ አገር፣ እርሱም የአውራጃው ብቸኛ ገዥ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌቤር የተባለው የኡሪ ልጅ፦ በአሞራውያን ንጉሥ ሲሖንና በባሳን ንጉሥ ዖግ ትገዛ የነበረችው የገለዓድ ግዛት አስተዳዳሪ። እነዚህን ዐሥራ ሁለቱን አስተዳዳሪዎች የሚቆጣጠር በመላ አገሪቱ ሌላ አንድ የበላይ ኀላፊ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጌቤር የተባለው የኡሪ ልጅ፦ በአሞራውያን ንጉሥ ሲሖንና በባሳን ንጉሥ ዖግ ትገዛ የነበረችው የገለዓድ ግዛት አስተዳዳሪ። እነዚህን ዐሥራ ሁለቱን አስተዳዳሪዎች የሚቈጣጠር በመላ አገሪቱ ሌላ አንድ የበላይ ኀላፊ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በአሞራውያን ንጉሥ በሴዎንና በባሳን ንጉሥ በዐግ አገር፥ በገለዓድ አገር፥ የኡሪ ልጅ ጌበር ነበረ፤ በዚያችም ምድር ላይ እርሱ ብቻውን ሹም ነበረ። |
“ከቄድሞትም ምድረ በዳ የሰላምን ቃል ይነግሩት ዘንድ ወደ ሐሴቦን ንጉሥ ወደ ሴዎን እንዲህ ብዬ መልእክተኞችን ላክሁ፦
“በዚያም ዘመን ከአርኖን ሸለቆ ጀምሮ እስከ ኤርሞን ድረስ ምድሪቱን በዮርዳኖስ ማዶ ከነበሩ ከሁለቱ ከአሞሬዎን ነገሥታት እጅ ወሰድን፤
የእስራኤልም ልጆች የመቱአቸው፥ ከአርኖንም ሸለቆ ጀምሮ እስከ አርሞንዔም ተራራ ድረስ በምሥራቅ በኩል ያለውን ዓረባ ሁሉ በዮርዳኖስም ማዶ በፀሐይ መውጫ ያለውን ሀገራቸውን የወረሱአቸው የምድር ነገሥት እነዚህ ናቸው፤
የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴና የእስራኤል ልጆች ገደሉአቸው፤ የእግዚአብሔርም አገልጋይ ሙሴ ርስት አድርጎ ለሮቤል ልጆች፥ ለጋድም ልጆች፥ ለምናሴም ነገድ እኩሌታ ምድሪቱን ሰጣቸው።