ዔሳውም አርባ ዓመት ሲሆነው የኬጢያዊው የብኤልን ልጅ ዮዲትን፥ የኬጢያዊው የኤሎንን ልጅ ቤሴሞትንም ሚስቶች አድርጎ አገባ፤
1 ነገሥት 4:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በንፍታሌምም አኪማኦስ ነበረ፤ እርሱም የሰሎሞንን ልጅ ባሴማትን አግብቶ ነበር፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም አኪማአስ በንፍታሌም፣ እርሱም የሰሎሞንን ልጅ ባስማትን አግብቶ የነበረ ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከሰሎሞን ሴቶች ልጆች መካከል ባስማት ተብላ የምትጠራውን አግብቶ የነበረ አሒመዓጽ፦ የንፍታሌም ግዛት አስተዳዳሪ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከሰሎሞን ሴቶች ልጆች መካከል ባስማት ተብላ የምትጠራውን አግብቶ የነበረ አሒመዓጽ፦ የንፍታሌም ግዛት አስተዳዳሪ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በንፍታሌም አኪማአስ ነበረ፤ እርሱም የሰሎሞንን ልጅ ባስማትን አግብቶ ነበር፤ |
ዔሳውም አርባ ዓመት ሲሆነው የኬጢያዊው የብኤልን ልጅ ዮዲትን፥ የኬጢያዊው የኤሎንን ልጅ ቤሴሞትንም ሚስቶች አድርጎ አገባ፤
ንጉሡም ደግሞ ካህኑን ሳዶቅን፥ “እነሆ፥ አንተና ልጅህ አኪማኦስ፥ የአብያታርም ልጅ ዮናታን፥ ሁለቱ ልጆቻችሁ ከእናንተ ጋር በሰላም ወደ ከተማ ተመለሱ።
ዳዊትም ሳኦልን፥ “ለንጉሥ አማች እሆን ዘንድ እኔ ማን ነኝ? ሰውነቴስ ምንድን ናት? የአባቴስ ወገን በእስራኤል ዘንድ ምንድን ነው?” አለው።