La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ነገሥት 22:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ሚክ​ያ​ስ​ንም ሊጠራ የሄደ መል​እ​ክ​ተኛ፥ “እነሆ፥ ነቢ​ያት ሁሉ በአ​ንድ አፍ ሆነው ለን​ጉሡ መል​ካ​ምን ይና​ገ​ራሉ፤ ቃል​ህም እንደ ቃላ​ቸው እን​ዲ​ሆን መል​ካም እን​ድ​ት​ና​ገር እለ​ም​ን​ሃ​ለሁ” አለው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ሚክያስን ሊጠራ ሄዶ የነበረውም መልእክተኛ፣ “እነሆ፣ ሌሎቹ ነቢያት በአንድ አፍ ሆነው፣ ለንጉሡ መልካምን ነገር እየተነበዩ ነው፤ እባክህ የአንተም ቃል እንደ ቃላቸው ይሁን፤ ንጉሡን ደስ የሚያሠኘውን ተናገር” አለው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ሚክያስን ለመጥራት ሄዶ የነበረው መልእክተኛ በዚሁ ጊዜ ሚክያስን “ሌሎቹ ነቢያት በሙሉ ንጉሥ አክዓብ ድል የሚያደርግ መሆኑን የሚያረጋግጥ የትንቢት ቃል ተናግረዋል፤ ስለዚህም አንተም እንደ እነርሱ ብታደርግ ይሻልሃል” አለው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ሚክያስን ለመጥራት ሄዶ የነበረው መልእክተኛ በዚሁ ጊዜ ሚክያስን “ሌሎቹ ነቢያት በሙሉ ንጉሥ አክዓብ ድል የሚያደርግ መሆኑን የሚያረጋግጥ የትንቢት ቃል ተናግረዋል፤ ስለዚህም አንተም እንደእነርሱ ብታደርግ ይሻልሃል” አለው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ሚክያስንም ሊጠራ የሄደ መልእክተኛ “እነሆ፥ ነቢያት ሁሉ በአንድ አፍ ሆነው ለንጉሡ መልካምን ይናገራሉ፤ ቃልህም እንደ ቃላቸው እንዲሆን መልካም እንድትናገር እለምንሃለሁ፤” አለው።

Ver Capítulo



1 ነገሥት 22:13
12 Referencias Cruzadas  

ነቢ​ያ​ትም ሁሉ እን​ዲህ ብለው ትን​ቢት ተና​ገሩ፥ “ወደ ሬማት ዘገ​ለ​ዓድ ዝመት፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ይረ​ዳ​ሃል። ሶር​ያ​ው​ያ​ን​ንና ንጉ​ሣ​ቸ​ው​ንም በእ​ጅህ አሳ​ልፎ ይሰ​ጣ​ቸ​ዋል።”


ሚክ​ያ​ስም፥ “ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ነ​ግ​ረ​ኝን እር​ሱን እና​ገ​ራ​ለሁ” አለ።


አቤቱ፥ አድ​ነኝ፥ ደግ ሰው አል​ቆ​አ​ልና፥ ከሰው ልጆ​ችም መተ​ማ​መን ጐድ​ሎ​አ​ልና።


አቤቱ፥ በድ​ን​ኳ​ንህ ውስጥ ማን ያድ​ራል? በተ​ቀ​ደ​ሰ​ውም ተራ​ራህ ማን ይኖ​ራል?


ነገ​ሥ​ታቱ በክ​ፋ​ታ​ቸው፥ አለ​ቆ​ቹም በሐ​ሰ​ታ​ቸው ደስ ተሰኙ።


ነፋስንም ተከትሎ፦ ስለ ወይን ጠጅና ስለ ስካር ትንቢት እናገርልሃለሁ ብሎ ሐሰትን የሚናገር ሰው ቢኖር እርሱ ለዚህ ሕዝብ ነቢይ ይሆናል።