ንጉሡም ባለፈ ጊዜ ወደ እርሱ ጮኸ፥ “ባሪያህ ወደ ሰልፍ መካከል ወጣ፤ እነሆም፥ አንድ ሰው ፈቀቅ ብሎ ወደ እኔ መጣ፤ አንድ ሰውም አመጣና፦ ይህን ሰው ጠብቅ፤ ቢኰበልልም ነፍስህ በነፍሱ ፋንታ ትሆናለች፤ ወይም አንድ መክሊት ብር ትከፍላለህ አለኝ።
ንጉሡም ባለፈ ጊዜ ወደ እርሱ ጮኽ፦ ባሪያህ ወደ ሰልፍ መካከል ወጣ፤ እነሆም፥ አንድ ሰው ፈቀቅ ብሎ ወደ እኔ አንድ ሰው አመጣና፦ ይህን ሰው ጠብቅ፥ ቢኮበልልም ነፍስህ በነፍሱ ፋንታ ትሆናለች፥ ወይም አንድ መክሊት ብር ትከፍላለህ አለኝ።