የእስራኤልም ልጆች ተቈጠሩ፤ ሊገጥሙአቸውም ወጡ፤ የእስራኤልም ልጆች እንደ ሁለት ትናንሽ የፍየል መንጋዎች ሆነው በፊታቸው ሰፈሩ፤ ሶርያውያን ግን ምድርን ሞልተዋት ነበር።
1 ነገሥት 21:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእግዚአብሔርም ሰው መጥቶ የእስራኤልን ንጉሥ፥ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሶርያውያን፦ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር የተራሮች አምላክ ነው እንጂ የሸለቆ አምላክ አይደለም ብለዋልና ይህን ታላቅ ሠራዊት ሁሉ በእጅህ አሳልፌ እሰጠዋለሁ፤ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃለህ” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም እንዲህ የሚል የእግዚአብሔር ቃል ወደ ቴስብያዊው ወደ ኤልያስ መጣ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጌታም ሰው ቀርቦ “የእስራኤልን ንጉሥ፦ ጌታ እንዲህ ይላል፦ ሶርያውያን ጌታ የተራሮች አምላክ ነው እንጂ የሸለቆ አምላክ አይደለም ብለዋልና ይህን ታላቅ ጭፍራ ሁሉ በእጅህ አሳልፌ እሰጠዋለሁ፥ እኔም ጌታ እንደሆንሁ ታውቃላችሁ” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእግዚአብሔርም ቃል ወደ ቴስቢያዊው ወደ ኤልያስ እንዲህ ሲል መጣ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእግዚአብሔርም ሰው ቀርቦ የእስራኤልን ንጉሥ፦ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሶርያውያን፦ እግዚአብሔር የተራሮች አምላክ ነው እንጂ የሸለቆ አምላክ አይደለም ብለዋልና ይህን ታላቅ ጭፍራ ሁሉ በእጅህ አሳልፌ እሰጠዋለሁ፥ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ አለው። |
የእስራኤልም ልጆች ተቈጠሩ፤ ሊገጥሙአቸውም ወጡ፤ የእስራኤልም ልጆች እንደ ሁለት ትናንሽ የፍየል መንጋዎች ሆነው በፊታቸው ሰፈሩ፤ ሶርያውያን ግን ምድርን ሞልተዋት ነበር።
እነዚህም በእነዚያ ትይዩ ሰባት ቀን ያህል ሰፈሩ፤ በሰባተኛውም ቀን ተጋጠሙ፤ የእስራኤልም ልጆች ከሶርያውያን በአንድ ቀን መቶ ሺህ እግረኛ ገደሉ።
እግዚአብሔርም እንደ ተመለሱና እንደ ተፀፀቱ ባየ ጊዜ የእግዚአብሔር ቃል፥ “ከተመለሱ አላጠፋቸውም፤ ከጥቂት ቀንም በኋላ አድናቸዋለሁ፤ ቍጣዬም በኢየሩሳሌም ላይ አይፈስስም” ሲል ወደ ሰማያ መጣ።