1 ነገሥት 2:34 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የዮዳሄም ልጅ በንያስ ወጥቶ ያዘው፤ ገደለውም፤ በምድረ በዳም ባለው በራሱ ቤት ቀበረው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህም የዮዳሄ ልጅ በናያስ ወጣ፤ ኢዮአብንም መትቶ ገደለው፤ እርሱም በምድረ በዳ ባለው በገዛ ምድሩ ተቀበረ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ በናያ በታዘዘው መሠረት ኢዮአብን ገደለው፤ በቤቱም አጠገብ በሚገኘው በረሓ ተቀበረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ በናያ በታዘዘው መሠረት ኢዮአብን ገደለው፤ በቤቱም አጠገብ በሚገኘው በረሓ ተቀበረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የዮዳሄም ልጅ በናያስ ወጥቶ ወደቀበት፤ ገደለውም፤ በምድረ በዳም ባለው በቤቱ ተቀበረ። |
ንጉሡም አለው፥ “ሂድና እንደ ነገረህ አድርግ፤ ገድለህም ቅበረው፤ ኢዮአብም በከንቱ ያፈሰሰውን ደም ከእኔና ከአባቴ ቤት ታርቃለህ።
ቍጥሩ ከባሕር አሸዋ የሚበልጥ በደልን በድያለሁና፥ ኀጢአቴም ብዙ ነውና፤ ከበደሌም ብዛት የተነሣ ቀና ብዬ የሰማይን ርዝመት አይ ዘንድ አገባቤ አይደለም። ሰውነቴን ከኀጢአቴ አሳርፋት ዘንድ በብረት ቀፎ ደከምሁ፤ በዚህም ደግሞ አላረፍሁም፤ መዓትህን አነሣሥቻለሁና፥
እነርሱም፥ “አስረን በፍልስጥኤማውያን እጅ አሳልፈን ልንሰጥህ መጥተናል” አሉት። ሶምሶንም፥ “እናንተ እንዳትገድሉኝ ማሉልኝ፤ ለእነርሱም አሳልፋችሁ ስጡኝ፤ እናንተ ግን ከእኔ ጋር አትዋጉ” አላቸው።