እርስዋም ኤልያስን፥ “የእግዚአብሔር ሰው ሆይ፥ እኔ ከአንተ ጋር ምን አለኝ? አንተስ ከእኔ ጋር ምን አለህ? ኀጢአቴንስ ታሳስብ ዘንድ፥ ልጄንስ ትገድል ዘንድ ወደ እኔ መጥተሃልን?” አለችው።
1 ነገሥት 18:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አብድዩም አለ፥ “እኔን አገልጋይህን እንዲገድለኝ በአክዓብ እጅ አሳልፈህ ትሰጠኝ ዘንድ ምን በደልሁ? አዲሱ መደበኛ ትርጒም አብድዩም እንዲህ አለው፤ “ምነው ምን አጠፋሁና ነው ባሪያህ እንዲሞት ለአክዓብ አሳልፈህ የምትሰጠው? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አብድዩም እንዲህ አለው፤ “ንጉሥ አክዓብ እኔን ባርያህን ይገድለኝ ዘንድ በእጁ አሳልፈህ የምትሰጠኝ ምን በደል ሠርቼ ነው? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አብድዩም እንዲህ አለው፤ “ንጉሥ አክዓብ እኔን ባሪያህን ይገድለኝ ዘንድ በእጁ አሳልፈህ የምትሰጠኝ ምን በደል ሠርቼ ነው? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አብድዩም አለ “እኔን ባሪያህን እንዲገድል በአክዓብ እጅ አሳልፈህ ትሰጠኝ ዘንድ ምን ኀጢአት አድርጌአለሁ? |
እርስዋም ኤልያስን፥ “የእግዚአብሔር ሰው ሆይ፥ እኔ ከአንተ ጋር ምን አለኝ? አንተስ ከእኔ ጋር ምን አለህ? ኀጢአቴንስ ታሳስብ ዘንድ፥ ልጄንስ ትገድል ዘንድ ወደ እኔ መጥተሃልን?” አለችው።
አምላክህ ሕያው እግዚአብሔርን! ጌታዬ፥ ይፈልግህ ዘንድ ያልላከበት ሕዝብ ወይም መንግሥት የለም፤ ሁሉም፦ በዚህ የለም ባሉ ጊዜ አንተን እንዳላገኙ መንግሥቱንና ሕዝቡን አምሎአቸው ነበር።
እኔም ከአንተ ጥቂት ራቅ ስል የእግዚአብሔር መንፈስ አንሥቶ ወደማላውቀው ስፍራ ይወስድሃል፤ እኔም ገብቼ ለአክዓብ ስናገር፥ ባያገኝህ ይገድለኛል፤ እኔም ባሪያህ ከትንሽነቴ ጀምሬ እግዚአብሔርን እፈራ ነበር።
እነርሱም፥ “በፈርዖንና በሹሞቹ ፊት ሽታችንን አግምታችሁታልና፥ ይገድለንም ዘንድ ሰይፍን በእጁ ሰጥታችሁታልና እግዚአብሔር ይመልከታችሁ፤ ይፍረድባችሁም” አሉአቸው።