1 ነገሥት 17:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከብዙ ቀንም በኋላ በምድር ላይ ዝናብ አልነበረምና ፈፋው ደረቀ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በምድሪቱ ላይ ዝናብ ባለመጣሉ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ወንዙ ደረቀ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዝናብ ጠፍቶ ድርቅ ከመሆኑ የተነሣ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ያ ወንዝ ደረቀ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዝናብ ጠፍቶ ድርቅ ከመሆኑ የተነሣ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ያ ወንዝ ደረቀ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከብዙ ቀንም በኋላ በምድር ላይ ዝናብ አልነበረምና ወንዙ ደረቀ። |
ተራሮችን እንዳልቀሥፋቸው እንዳላፈልሳቸውም፥ ኮረብቶችም እንዳይነዋወጡ እንደ ማልሁ እንዲሁ ከእኔ ዘንድ ያለሽ ይቅርታ አያልቅም፤ የሰላምሽ ቃል ኪዳንም አይጠፋም፤ መሓሪሽ እግዚአብሔር ይህን ተናግሮአልና።
እግዚአብሔር በክሳት፥ በንዳድም፥ በጥብሳትም፥ በትኵሳትም፥ በድርቅም፥ በዋግም፥ በአረማሞም ይመታሃል፤ እስክትጠፋም ድረስ ያሳድዱሃል።