ከዛፉም ሥር ዕረፉ፤ እንጀራም እናምጣላችሁና ብሉ፤ ከዚያም በባሪያችሁ ዘንድ ከአረፋችሁ በኋላ፥ ወደ ዐሰባችሁት ትሄዳላችሁ።” እነርሱም፥ “እንዳልህ እንዲሁ አድርግ” አሉት።
1 ነገሥት 17:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ውኃም ልታመጣለት በሄደች ጊዜ ወደ እርስዋ ጠርቶ፥ “እግረ መንገድሽን ቍራሽ እንጀራ በእጅሽ አምጭልኝ” አላት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ልታመጣለት ስትሄድ አሁንም ጠራትና፣ “እባክሽን፣ ቍራሽ እንጀራም ይዘሽልኝ ነይ” አላት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ውሃም ልታመጣለት በመሄድ ላይ ሳለች ወዲያውኑ ጠርቶ “እባክሽ በተጨማሪ ትንሽ እንጀራ አምጪልኝ” አላት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ውሃም ልታመጣለት በመሄድ ላይ ሳለች ወዲያውኑ ጠርቶ “እባክሽ በተጨማሪ ትንሽ እንጀራ አምጪልኝ” አላት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ውሃም ልታመጣለት በሄደች ጊዜ ወደ እርስዋ ጠርቶ “ቍራሽ እንጀራ በእጅሽ ይዘሽ ትመጭ ዘንድ እለምንሻለሁ፤” አላት። |
ከዛፉም ሥር ዕረፉ፤ እንጀራም እናምጣላችሁና ብሉ፤ ከዚያም በባሪያችሁ ዘንድ ከአረፋችሁ በኋላ፥ ወደ ዐሰባችሁት ትሄዳላችሁ።” እነርሱም፥ “እንዳልህ እንዲሁ አድርግ” አሉት።
ተነሥቶም ወደ ሰራፕታ ሄደ፤ ወደ ከተማዪቱም በር በደረሰ ጊዜ አንዲት መበለት በዚያ እንጨት ትለቅም ነበር፤ ኤልያስም ጠርቶ፥ “የምጠጣው ጥቂት ውኃ በጽዋ ታመጭልኝ ዘንድ እለምንሻለሁ” አላት።
ሴትየዋም፥ “አምላክህ ሕያው እግዚአብሔርን! በማድጋ ካለው ከእፍኝ ዱቄት በማሰሮም ካለው ከጥቂት ዘይት በቀር እንጀራ የለኝም፤ እነሆም፥ ጥቂት እንጨት እሰበስባለሁ፤ ሄጄም ለእኔና ለልጄ እጋግረዋለሁ፤ በልተነውም እንሞታለን” አለችው።
“ተነሥተህ በሲዶና አጠገብ ወዳለችው ወደ ሰራፕታ ሂድ፤ በዚያም ተቀመጥ፤ እነሆም፥ ትመግብህ ዘንድ አንዲት መበለት አዝዣለሁ።”
ኤልዛቤልም የእግዚአብሔርን ነቢያት ባስገደለች ጊዜ አብድዩ መቶውን ነቢያት ወስዶ አምሳ አምሳውን በዋሻ ውስጥ ሸሽጎ እንጀራና ውኃ ይመግባቸው ነበር።