La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ነገሥት 15:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ከእ​ር​ሱም አስ​ቀ​ድሞ ባደ​ረ​ገው በአ​ባቱ ኀጢ​አት ሁሉ ሄደ፤ ልቡም እንደ አባቱ እንደ ዳዊት ልብ ከአ​ም​ላኩ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጋር ፍጹም አል​ነ​በ​ረም።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እርሱም አባቱ ከርሱ በፊት የሠራውን ኀጢአት ሁሉ ሠራ፤ እንደ አባቱ እንደ ዳዊትም በፍጹም ልቡ በታማኝነት ለእግዚአብሔር አልተገዛም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

አቢያም፥ እንደ ታላቁ አያቱ እንደ ዳዊት በጌታ ዘንድ ፍጹም ታማኝ ሆኖ በመገኘት ፈንታ፥ አባቱ ሮብዓም ይፈጽመው የነበረውን ኃጢአት ሁሉ መሥራቱን ቀጠለ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

አቢያም፥ እንደ ታላቁ አያቱ እንደ ዳዊት በእግዚአብሔር ዘንድ ፍጹም ታማኝ ሆኖ በመገኘት ፈንታ፥ አባቱ ሮብዓም ይፈጽመው የነበረውን ኃጢአት ሁሉ መሥራቱን ቀጠለ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ከእርሱ አስቀድሞ ባደረገው በአባቱ ኀጢአት ሁሉ ሄደ፤ ልቡም እንደ አባቱ እንደ ዳዊት ልብ ከአምላኩ ከእግዚአብሔር ጋር ፍጹም አልነበረም።

Ver Capítulo



1 ነገሥት 15:3
12 Referencias Cruzadas  

ትቶ​ኛ​ልና፥ ለሲ​ዶ​ና​ው​ያ​ንም ርኵ​ሰት ለአ​ስ​ጠ​ራ​ጢስ፥ ለሞ​አ​ብም አም​ላክ ለኮ​ሞስ፥ ለአ​ሞ​ንም ልጆች አም​ላክ ለሞ​ሎክ ሰግ​ዶ​አ​ልና፥ አባ​ቱም ዳዊት እን​ዳ​ደ​ረገ በፊቴ ቅን ነገ​ርን ያደ​ርግ ዘንድ በመ​ን​ገ​ዶቼ አል​ሄ​ደ​ምና።


ከዚህ በኋላ ሰሎ​ሞን በሸ​መ​ገለ ጊዜ ልቡ እንደ አባቱ እንደ ዳዊት ልብ ከአ​ም​ላኩ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጋር አል​ነ​በ​ረም። ከባ​ዕድ ያገ​ባ​ቸው ሚስ​ቶ​ቹም ሌሎ​ችን አማ​ል​ክት ይከ​ተል ዘንድ ልቡን መለ​ሱት።


ነገር ግን በኮ​ረ​ብ​ቶች ላይ ያሉ​ትን መስ​ገ​ጃ​ዎች አላ​ራ​ቀም፤ የአሳ ልብ ግን በዘ​መኑ ሁሉ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጋር ፍጹም ነበረ።


አባ​ት​ህም ዳዊት እንደ ሄደ፥ ሥር​ዐ​ቴ​ንና ትእ​ዛ​ዜን ትጠ​ብቅ ዘንድ በመ​ን​ገዴ የሄ​ድህ እንደ ሆነ፥ ዘመ​ን​ህን አበ​ዛ​ል​ሀ​ለሁ።”


ሰሎ​ሞ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ይወ​ድድ ነበር፤ በአ​ባ​ቱም በዳ​ዊት ሥር​ዐት ይሄድ ነበር፤ ነገር ግን በኮ​ረ​ብ​ታው ላይ ይሠ​ዋና ያጥን ነበር።


“አቤቱ፥ በፊ​ትህ በእ​ው​ነ​ትና በፍ​ጹም ልብ እንደ ሄድሁ፥ መል​ካም ነገ​ርም እን​ዳ​ደ​ረ​ግሁ አስብ።” ሕዝ​ቅ​ያ​ስም እጅግ አለ​ቀሰ።


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ቅን ነገ​ርን አደ​ረገ፤ ነገር ግን በፍ​ጹም ልብ አይ​ደ​ለም።


ልቡ በወ​ን​ድ​ሞቹ ላይ እን​ዳ​ይ​ኰራ፥ የአ​ም​ላኩ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛዝ እን​ዳ​ይ​ተው፥ ቀኝና ግራም እን​ዳ​ይል፥ እር​ሱም ልጆ​ቹም በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መካ​ከል ረዥም ዘመን ይገዙ ዘንድ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለጌ​ታዬ የታ​መነ ቤትን ይሠ​ራ​ለ​ታ​ልና፥ የጌ​ታ​ዬ​ንም ጦር​ነት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይዋ​ጋ​ለ​ታ​ልና የእ​ኔን የባ​ሪ​ያ​ህን ኀጢ​ኣት፥ እባ​ክህ፥ ይቅር በል፤ በዘ​መ​ን​ህም ሁሉ ክፋት አይ​ገ​ኝ​ብ​ህም።