ሰሎሞንም ኢዮርብዓምን ሊገድለው ወደደ፤ ኢዮርብዓምም ተነሥቶ ወደ ግብፅ ሀገር፥ ወደ ግብፅ ንጉሥ ወደ ሱስቀም ኰብልሎ ሄደ፥ ሰሎሞንም እስኪሞት ድረስ በግብፅ ተቀመጠ።
1 ነገሥት 14:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሮብዓምም በነገሠ በአምስተኛው ዓመት የግብፅ ንጉሥ ሱስቀም በኢየሩሳሌም ላይ ዘመተ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሮብዓም በነገሠ በዐምስተኛው ዓመት፣ የግብጽ ንጉሥ ሺሻቅ በኢየሩሳሌም ላይ ዘመተ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሮብዓም በነገሠ በአምስተኛው ዓመት የግብጽ ንጉሥ ሺሻቅ በኢየሩሳሌም ላይ አደጋ ጣለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሮብዓም በነገሠ በአምስተኛው ዓመት የግብጽ ንጉሥ ሺሻቅ በኢየሩሳሌም ላይ አደጋ ጣለ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሮብዓምም በነገሠ በአምስተኛው ዓመት የግብጽ ንጉሥ ሺሻቅ በኢየሩሳሌም ላይ መጣ። |
ሰሎሞንም ኢዮርብዓምን ሊገድለው ወደደ፤ ኢዮርብዓምም ተነሥቶ ወደ ግብፅ ሀገር፥ ወደ ግብፅ ንጉሥ ወደ ሱስቀም ኰብልሎ ሄደ፥ ሰሎሞንም እስኪሞት ድረስ በግብፅ ተቀመጠ።
የግብፅ ንጉሥ ሱስቀምም ወደ ኢየሩሳሌም መጣ፤ የእግዚአብሔርንም ቤተ መዛግብትና የንጉሡን ቤተ መዛግብት ወሰደ፤ ሁሉንም ወሰደ፤ ደግሞም ሰሎሞን የሠራቸውን የወርቁን አላባሽ አግሬ ጋሻዎችን ወሰደ።