1 ነገሥት 13:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም፥ “ከአንተ ጋር እመለስና እገባ ዘንድ አይቻለኝም፤ በዚህም ስፍራ ከአንተ ጋር እንጀራ አልበላም፤ ውኃም አልጠጣም፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእግዚአብሔርም ሰው እንዲህ ሲል መለሰለት፤ “ተመልሼ ከአንተ ጋራ አልሄድም፤ በዚህ ቦታም ዐብሬህ እንጀራ አልበላም፤ ውሃም አልጠጣም፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም እንዲህ ሲል መለሰለት፦ “ከአንተ ጋር አብሬ መመለስ አልችልም፤ በዚህም ከአንተ ጋር ምንም ዓይነት እህልም ውሃም አልቀምስም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከይሁዳ የመጣው የእግዚአብሔር ነቢይ ግን እንዲህ ሲል መለሰለት፤ “ከአንተ ጋር አብሬ ወደ ቤት መሄድም ሆነ ግብዣህን መቀበል አልችልም፤ በዚህም ከአንተ ጋር ምንም ዐይነት እህል ውሃ አልቀምስም፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም “ከአንተ ጋር እመለስና እገባ ዘንድ አይቻለኝም፤ በዚህም ስፍራ ከአንተ ጋር እንጀራ አልበላም፤ ውሃም አልጠጣም፤ |
በለዓምም ሲነጋ ተነሥቶ የባላቅን አለቆች፥ “ከእናንተ ጋር እሄድ ዘንድ እግዚአብሔር አልፈቀደልኝምና ወደ ጌታችሁ ሂዱ” አላቸው።
እርሱ ግን ዘወር ብሎ ጴጥሮስን “ወደ ኋላዬ ሂድ፤ አንተ ሰይጣን! የሰውን እንጂ የእግዚአብሔርን አታስብምና፥ ዕንቅፋት ሆነህብኛል፤” አለው።