ሜምፌቡስቴም አለ፥ “ጌታዬ፥ ንጉሥ፥ አገልጋዬ አታለለኝ፥ እኔ ባሪያህ አንካሳ ነኝና፦ ከንጉሡ ጋር እሄድ ዘንድ አህያዬን ጫንልኝ፤ እኔም እቀመጥበታለሁ አልሁት።
1 ነገሥት 13:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ልጆቹንም፥ “አህያዬን ጫኑልኝ” አላቸው፥ አህያውንም ጫኑለት ተቀመጠበትም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህም ልጆቹን፣ “በሉ አህያውን ጫኑልኝ” አላቸው። እነርሱም አህያውን ጫኑለትና ተቀምጦበት መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚህም በኋላ እርሱ “አህያዬን ጫኑልኝ!” አላቸው፤ ልጆቹም አህያውን ጭነውለት ሽማግሌው ነቢይ በአህያው ላይ ተቀምጦ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህም በኋላ እርሱ “አህያዬን ጫኑልኝ!” አላቸው፤ ልጆቹም አህያውን ጭነውለት ሽማግሌው ነቢይ በአህያው ላይ ተቀምጦ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ልጆቹንም “አህያውን ጫኑልኝ፤” አላቸው፤ አህያውንም በጫኑለት ጊዜ ተቀመጠበት። |
ሜምፌቡስቴም አለ፥ “ጌታዬ፥ ንጉሥ፥ አገልጋዬ አታለለኝ፥ እኔ ባሪያህ አንካሳ ነኝና፦ ከንጉሡ ጋር እሄድ ዘንድ አህያዬን ጫንልኝ፤ እኔም እቀመጥበታለሁ አልሁት።
አባታቸውም፥ “በየትኛው መንገድ ሄደ?” አላቸው። ልጆቹም ከይሁዳ የመጣው የእግዚአብሔር ሰው የሄደበትን መንገድ አመለከቱት።
የእግዚአብሔርንም ሰው ተከትሎት ሄደ፤ ከዛፍ በታችም ተቀምጦ አገኘውና፥ “ከይሁዳ የመጣህ የእግዚአብሔር ሰው አንተ ነህን?” አለው። እርሱም፥ “አዎ፥ እኔ ነኝ” አለ።
በሠላሳ ሁለት የአህያ ግልገሎች ይቀመጡ የነበሩ ሠላሳ ሁለት ልጆችም ነበሩት፤ ለእነርሱም እስከ ዛሬ ድረስ የኢያዕር መንደሮች የተባሉ በገለዓድ ምድር ያሉ ሠላሳ ሁለት ከተሞች ነበሩአቸው።