1 ነገሥት 13:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በቤቴልም አንድ ሽማግሌ ነቢይ ይኖር ነበር፤ ልጆቹም ወደ እርሱ መጥተው በዚያች ቀን የእግዚአብሔር ሰው በቤቴል ያደረገውን ሥራ ሁሉ ነገሩት፤ ደግሞም ለንጉሡ የተናገረውን ቃል ሁሉ ለአባታቸው ነገሩት፤ አባታቸውም ተቈጣቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያ ጊዜ በቤቴል የሚኖር አንድ ሽማግሌ ነቢይ ነበር፤ ልጆቹም መጥተው በዚያች ዕለት የእግዚአብሔር ሰው እዚያ ያደረገውን ሁሉና ንጉሡንም ምን እንዳለው ለአባታቸው ነገሩት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያን ጊዜ በቤትኤል የሚኖር አንድ ሽማግሌ ነቢይ ነበር፤ ወንዶች ልጆቹ ወደ እርሱ ቀርበው፥ ከይሁዳ የመጣው ነቢይ በቤትኤል ስላደረገውና በንጉሥ ኢዮርብዓምም ላይ ስለ ተናገረው ቃል ሁሉ አወሩለት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያን ጊዜ በቤትኤል የሚኖር አንድ ሽማግሌ ነቢይ ነበር፤ ወንዶች ልጆቹ ወደ እርሱ ቀርበው፥ ከይሁዳ የመጣው ነቢይ በቤትኤል ስላደረገውና በንጉሥ ኢዮርብዓምም ላይ ስለ ተናገረው ቃል ሁሉ አወሩለት፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በቤቴልም አንድ ሽማግሌ ነቢይ ይቀመጥ ነበር፤ ልጆቹም ወደ እርሱ መጥተው በዚያ ቀን የእግዚአብሔር ሰው በቤቴል ያደረገውን ሥራ ሁሉ ነገሩት፤ ደግሞም ለንጉሡ የተናገረውን ቃል ሁሉ ለአባታቸው ነገሩት። |
አባታቸውም፥ “በየትኛው መንገድ ሄደ?” አላቸው። ልጆቹም ከይሁዳ የመጣው የእግዚአብሔር ሰው የሄደበትን መንገድ አመለከቱት።
እነሆም፥ መንገድ አላፊ ሰዎች ሬሳውን በመንገዱ ወድቆ፥ አንበሳውም በሬሳው አጠገብ ቆሞ አዩ፤ ገብተውም ሽማግሌው ነቢይ ይኖርበት በነበረው ከተማ አወሩ።
እነርሱም ስለ ኢየሩሳሌም ትንቢት የሚናገሩ፥ የሰላምንም ራእይ የሚያዩላት የእስራኤል ነቢያት ናቸው፤ ሰላምም የለም፥” ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
“የሰው ልጅ ሆይ! ትንቢት በሚናገሩ በእስራኤል ነቢያት ላይ ትንቢት ተናገር፤ ከገዛ ልባቸውም ትንቢት የሚናገሩትን፦ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ በላቸው፤
በዚያ ቀን ብዙዎች ‘ጌታ ሆይ! ጌታ ሆይ! በስምህ ትንቢት አልተናገርንምን? በስምህስ አጋንንትን አላወጣንምን? በስምህስ ብዙ ተአምራትን አላደረግንምን?’ ይሉኛል።
ቀድሞም የሚያውቁት ሁሉ በነቢያት መካከል ባዩት ጊዜ ሕዝቡ እርስ በርሳቸው፥ “በቂስ ልጅ ላይ የሆነው ምንድን ነው? በውኑ ሳኦል ከነቢያት ወገን ነውን?” ተባባሉ።