ያችም ሴት አለች፥ “መልካሙንና ክፉውን ነገር ለመስማት ንጉሡ ጌታዬ እንደ መሥዋዕትና እንደ እግዚአብሔር መልአክ ነውና የጌታዬ የንጉሡ ቃል እንደዚሁ ነው፤ አምላክህም እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ይሁን።”
1 ነገሥት 10:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰሎሞንም የጠየቀችውን ሁሉ ፈታላት፤ ያልተረጐመላትና ከንጉሡ የተሰወረ ነገር አልነበረም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰሎሞንም የጠየቀችውን ሁሉ መለሰላት፤ ከንጉሡ የተሰወረና ሊመልስላት ያልቻለው አንድም ጥያቄ አልነበረም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም ላቀረበችለት ጥያቄ ሁሉ መልስ ሰጠ፤ ሊተረጉምላት የተሳነውና ከእርሱ የተሰወረ ምንም ዓይነት እንቆቅልሽ አልነበረም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱም ላቀረበችለት ጥያቄ ሁሉ መልስ ሰጠ፤ ሊተረጒምላት የተሳነውና ከእርሱ የተሰወረ ምንም ዐይነት እንቆቅልሽ አልነበረም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰሎሞንም የጠየቀችውን ሁሉ ፈታላት፤ ሊፈታላት ያልቻለውና ከንጉሡ የተሰወረ ነገር አልነበረም። |
ያችም ሴት አለች፥ “መልካሙንና ክፉውን ነገር ለመስማት ንጉሡ ጌታዬ እንደ መሥዋዕትና እንደ እግዚአብሔር መልአክ ነውና የጌታዬ የንጉሡ ቃል እንደዚሁ ነው፤ አምላክህም እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ይሁን።”
ይህን ነገር እናገር ዘንድ እንድመጣ ይህን ምክር ያደረገ አገልጋይህ ኢዮአብ ነው። ጌታዬ ግን በዚህ ዓለም የሚደረገውን ሁሉ ታውቅ ዘንድ እንደ መልአከ እግዚአብሔር ጥበብ ጥበበኛ ነህ፤”
የሳባም ንግሥት የሰሎሞንን ስም፥ የእግዚአብሔርንም ስም በሰማች ጊዜ ሰሎሞንን በእንቆቅልሽ ትፈትነው ዘንድ መጣች።
በግመሎችም ላይ ሽቱና እጅግ ብዙ ወርቅ የከበረም ዕንቍ አስጭና ከታላቅ ጓዝ ጋር ወደ ኢየሩሳሌም ገባች፤ ወደ ሰሎሞንም በመጣች ጊዜ በልብዋ ያለውን ሁሉ ነገረችው።
እነሆ፥ እኔ እንደ ቃልህ አድርጌልሃለሁ፤ እነሆም፥ ማንም የሚመስልህ ከአንተ በፊት እንደሌለ፥ ከአንተም በኋላ እንዳይነሣ አድርጌ ጥበበኛና አስተዋይ ልቡና ሰጥቼሃለሁ።
ዕውሮችንም በማያውቋት መንገድ አመጣቸዋለሁ፤ የማያውቋትንም ጎዳና እንዲረግጡ አደርጋቸዋለሁ፤ በፊታቸውም ጨለማውን ብርሃን አደርጋለሁ፤ ጠማማውንም አቀናለሁ። ይህንም አደርግላቸዋለሁ፤ አልተዋቸውምም።
ፈቃዱን ሊያደርግ የሚወድድ ግን ትምህርቴ ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደ ሆነች፥ የምናገረውም ከራሴ እንዳይደለ እርሱ ያውቃል።
እናንተም በኢየሱስ ክርስቶስ ከእርሱ ናችሁ፤ በእርሱም ከእግዚአብሔር ጥበብንና ጽድቅን፥ ቅድስናንና ቤዛነትን አገኘን።