ዳዊትም ለሱባን ንጉሥ ለአድርአዛር አገልጋዮች የነበሩትን ጋሻ አግሬዎች ወሰደ፤ ወደ ኢየሩሳሌምም አመጣቸው። እነዚህንም የግብፅ ንጉሥ ሱስቀም በሰሎሞን ልጅ በሮብዓም ዘመን ወደ ኢየሩሳሌም በወጣ ጊዜ ወሰዳቸው።
1 ነገሥት 10:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ንጉሡ ሰሎሞንም ከጥፍጥፍ ወርቅ ሁለት መቶ አላባሽ አግሬ ጋሻ አሠራ፤ በአንዱም አላባሽ አግሬ ጋሻ ውስጥ የገባው ወርቅ ሦስት መቶ ሰቅል ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ንጉሥ ሰሎሞን ከጥፍጥፍ ወርቅ ሁለት መቶ ትላልቅ ጋሻዎችን አበጀ፤ በእያንዳንዱም ጋሻ የገባው ስድስት መቶ ሰቅል ጥፍጥፍ ወርቅ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ንጉሥ ሰሎሞን ሁለት መቶ ታላላቅ ጋሻዎችን አሠርቶ እያንዳንዱን ጋሻ በሰባት ኪሎ ያኽል ወርቅ አስለበጠው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሥ ሰሎሞን ሁለት መቶ ታላላቅ ጋሻዎችን አሠርቶ እያንዳንዱን ጋሻ በሰባት ኪሎ ያኽል ወርቅ አስለበጠው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንጉሡም ሰሎሞን ከጥፍጥፍ ወርቅ ሁለት መቶ አላባሽ አግሬ ጋሻ አሠራ፤ በአንዱም አላባሽ አግሬ ጋሻ ውስጥ የገባው ወርቅ ስድስት መቶ ሰቅል ነበረ። |
ዳዊትም ለሱባን ንጉሥ ለአድርአዛር አገልጋዮች የነበሩትን ጋሻ አግሬዎች ወሰደ፤ ወደ ኢየሩሳሌምም አመጣቸው። እነዚህንም የግብፅ ንጉሥ ሱስቀም በሰሎሞን ልጅ በሮብዓም ዘመን ወደ ኢየሩሳሌም በወጣ ጊዜ ወሰዳቸው።