1 ነገሥት 1:32 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ንጉሡም ዳዊት፥ “ካህኑን ሳዶቅንና ነቢዩ ናታንን የዮዳሄንም ልጅ በናያስን ጥሩልኝ” አለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ንጉሥ ዳዊትም፣ “ካህኑን ሳዶቅን፣ ነቢዩን ናታንንና የዮዳሄን ልጅ በናያስን ጥሩልኝ” አለ። እነርሱም ንጉሡ ፊት በቀረቡ ጊዜ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ንጉሡም ዳዊት፦ “ካህኑን ሳዶቅንና ነቢዩን ናታንን የዮዳሄንም ልጅ በናያስን ጥሩልኝ” አለ። ወደ ንጉሡም ፊት ገቡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ንጉሥ ዳዊት ካህኑን ሳዶቅን፥ ነቢዩን ናታንንና የዮዳሄን ልጅ በናያን አስጠራ፤ እነርሱም ገብተው ወደ እርሱ ቀረቡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንጉሡም ዳዊት “ካህኑን ሳዶቅንና ነቢዩን ናታንን የዮዳሄንም ልጅ በናያስን ጥሩልኝ፤” አለ። ወደ ንጉሡም ፊት ገቡ። |
ነገር ግን እኔን አገልጋይህን፥ ካህኑንም ሳዶቅን፥ የዮዳሄንም ልጅ በናያስን፥ አገልጋይህንም ሰሎሞንን አልጠራም።
ካህኑም ሳዶቅና ነቢዩ ናታን የዮዳሄም ልጅ በናያስ ከሊታውያንና ፈሊታውያንም ወረዱ፤ ሰሎሞንንም በንጉሡ በዳዊት በቅሎ ላይ አስቀምጠው ወደ ግዮን ወሰዱት።
ነገር ግን ካህኑ ሳዶቅና የዮዳሄ ልጅ በናያስ ነቢዩም ናታን፥ ሳሚም፥ ሬሲም፥ የዳዊትም ኀያላን አዶንያስን አልተከተሉም ነበር።