La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ነገሥት 1:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ናታ​ንም የሰ​ሎ​ሞ​ንን እናት ቤር​ሳ​ቤ​ህን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ራት፥ “ጌታ​ችን ዳዊት ሳያ​ውቅ የአ​ጊት ልጅ አዶ​ን​ያስ እንደ ነገሠ አል​ሰ​ማ​ሽ​ምን?

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከዚያም ናታን የሰሎሞንን እናት ቤርሳቤህን እንዲህ አላት፤ “ጌታችን ዳዊት ሳያውቅ የአጊት ልጅ አዶንያስ መንገሡን አልሰማሽምን?

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ናታንም የሰሎሞንን እናት ቤርሳቤህን እንዲህ ብሎ ተናገራት፦ “ጌታችን ዳዊት ሳያውቅ የሐጊት ልጅ አዶንያስ እንደ ነገሠ አልሰማሽምን?

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከዚህ በኋላ ናታን ወደ ሰሎሞን እናት ወደ ቤርሳቤህ ሄዶ “ጌታችን ዳዊት ሳያውቅ የሐጊት ልጅ አዶንያስ መንገሡን አልሰማሽምን?” አላት።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ናታንም የሰሎሞንን እናት ቤርሳቤህን እንዲህ ብሎ ተናገራት “ጌታችን ዳዊት ሳያውቅ የአጊት ልጅ አዶንያስ እንደ ነገሠ አልሰማሽምን?

Ver Capítulo



1 ነገሥት 1:11
9 Referencias Cruzadas  

አቤ​ሴ​ሎ​ምም፥ “የመ​ለ​ከት ድምፅ በሰ​ማ​ችሁ ጊዜ፥ አቤ​ሴ​ሎም በኬ​ብ​ሮን ነገሠ” በሉ የሚሉ ጕበ​ኞ​ችን ወደ እስ​ራ​ኤል ነገድ ሁሉ ላከ።


አራ​ተ​ኛ​ውም የአ​ጊት ልጅ አዶ​ን​ያስ፥ አም​ስ​ተ​ኛ​ውም የአ​ቢ​ጣል ልጅ ሰፋ​ጥያ ነበረ።


ነገር ግን ነቢ​ዩን ናታ​ንን፥ በና​ያ​ስ​ንም፥ ኀያ​ላ​ኑ​ንም፥ ወን​ድ​ሙ​ንም ሰሎ​ሞ​ንን አል​ጠ​ራም።


የአ​ጊት ልጅ አዶ​ን​ያ​ስም ወደ ሰሎ​ሞን እናት ወደ ቤር​ሳ​ቤህ መጣ፤ ሰገ​ደ​ላ​ትም፤ እር​ስ​ዋም፥ “ወደ እኔ መም​ጣ​ትህ በሰ​ላም ነውን?” አለ​ችው። እር​ሱም፥ “በሰ​ላም ነው” አለ።


ንጉሡ ዳዊ​ትም ለጉ​ባ​ኤው ሁሉ እን​ዲህ አለ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ብቻ​ውን የመ​ረ​ጠው ልጄ ሰሎ​ሞን ገና ለጋ ብላ​ቴና ነው፤ ሕን​ጻው ግን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለአ​ም​ላክ ነው እንጂ ለሰው አይ​ደ​ለ​ምና ሥራው ታላቅ ነው።