La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ዮሐንስ 4:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ በሚታመን ሁሉ እግዚአብሔር በእርሱ ይኖራል እርሱም በእግዚአብሔር ይኖራል።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ አምኖ በሚመሰክር ሁሉ፣ እግዚአብሔር በርሱ ይኖራል፤ እርሱም በእግዚአብሔር ይኖራል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ የሚመሰክር ሁሉ፥ እግዚአብሔር በእርሱ ይኖራል እርሱም በእግዚአብሔር ይኖራል።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ በሚያምን ሰው ውስጥ እግዚአብሔር ይኖራል፤ እርሱም በእግዚአብሔር ይኖራል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ በሚታመን ሁሉ እግዚአብሔር በእርሱ ይኖራል እርሱም በእግዚአብሔር ይኖራል።

Ver Capítulo



1 ዮሐንስ 4:15
15 Referencias Cruzadas  

ስለዚህ በሰው ፊት ለሚመሰክርልኝ ሁሉ እኔ ደግሞ በሰማያት ባለው በአባቴ ፊት እመሰክርለታለሁ፤


“እላ​ች​ኋ​ለሁ፦ በሰው ፊት የሚ​ያ​ም​ን​ብ​ኝን ሁሉ እኔም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መላ​እ​ክት ፊት አም​ነ​ዋ​ለሁ።


ሥጋ​ዬን የሚ​በላ፥ ደሜ​ንም የሚ​ጠጣ በእኔ ይኖ​ራል፤ እኔም በእ​ርሱ እኖ​ራ​ለሁ።


ፊል​ጶ​ስም፥ “በፍ​ጹም ልብህ ብታ​ምን ይገ​ባ​ሃል” አለው፤ ጃን​ደ​ረ​ባ​ውም መልሶ፥ “ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጅ እንደ ሆነ እኔ አም​ና​ለሁ” አለው።


ኢየ​ሱስ ጌታ እንደ ሆነ በአ​ፍህ ብት​መ​ሰ​ክር እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከሙ​ታን ለይቶ እንደ አስ​ነ​ሣው በል​ብህ ብታ​ምን ትድ​ና​ለህ።


አን​ደ​በ​ትም ሁሉ ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አብ ክብር ጌታ እንደ ሆነ ያምን ዘንድ ነው።


ወልድን የሚክድ ሁሉ አብ እንኳ የለውም፤ በወልድ የሚታመን አብ ደግሞ አለው።


እናንተስ ከመጀመሪያ የሰማችሁት በእናንተ ጸንቶ ይኑር። ከመጀመሪያ የሰማችሁት በእናንተ ቢኖር፥ እናንተ ደግሞ በወልድና በአብ ትኖራላችሁ።


ትእዛዚቱም ይህች ናት፥ በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እናምን ዘንድ፥ ትእዛዝንም እንደ ሰጠን እርስ በርሳችን እንዋደድ ዘንድ።


ትእዛዙንም የሚጠብቅ በእርሱ ይኖራል እርሱም ይኖርበታል፤ በዚህም በእኛ እንዲኖር ከሰጠን ከመንፈሱ እናውቃለን።


እግዚአብሔርን ማንም ከቶ አላየውም፤ እርስ በርሳችን ብንዋደድ እግዚአብሔር በእኛ ይኖራል ፍቅሩም በእኛ ፍጹም ሆኖአል።


የእግዚአብሔርን መንፈስ በዚህ ታውቃላችሁ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ እንደ መጣ የሚታመን መንፈስ ሁሉ ከእግዚአብሔር ነው፥


ክርስቶስ ነው ብሎ በኢየሱስ የሚያምን ሁሉ ከእግዚአብሔር ተወልዶአል፥ ወላጁንም የሚወድ ሁሉ ከእርሱ የተወለደውን ደግሞ ይወዳል።


ኢየሱስም የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ ከሚያምን በቀር ዓለምን የሚያሸንፍ ማን ነው?


ብዙ አሳቾች ወደ ዓለም ገብተዋልና፤ እነርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ እንደ መጣ የማያምኑ ናቸው፤ ይህ አሳቹና የክርስቶስ ተቃዋሚው ነው።